ጥያቄና መልሶች

ይህ ገጽ ምንድን ነው?

ይህ ገጽ (ዳሽቦርድ) ለመዝሙር እና አውደ ምሕረት ሞባይል አፐልኬሽን ግባት የሚሆን ዳታ መሰብሰቢያ ነው:: ሦስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን ርዕሱን በመጫን መዘርጋት ወይም ወይም መሰብሰብ ያስችላል::

እንዴት ገብቼ መስራት እችላለሁ?

"Google Singin" የሚለውን በመጫን እና የጎግል ኢሜልና ማለፊያ ኮድ(password) ስታስገቡ ጎግል ትክክለኛ ተጠቃሚ መሆናችሁን በማረጋገጥ የይለፍ ማረጋገጫ ለአውደ ምሕረት ይልካል:: ከዚህ በኋላ ማንኛውንም ቁልፍ ብትጫኑ ይሰራል እንዴት መዝሙሩ እንዳለ ማረጋገጥ እችላለሁ?

በመዝሙር አፕ የሚገኙ መዝሙሮች ርዕስ ከፊት በሚታየው ሰንጠረዥ ላይ የሚገኝ ሲሆን ግጥሙ በጽሁፍ ወይም በስዕል መኖሩን በሰንጠረዙ 3ተኛ ክፍል Yes/No የሚለው ክፍል ይገልጻል:: መዝሙሩ በጽሁፍ መኖሩ በቀላሉ ለማንበብም ሆነ ለመፈለግ ስለሚረዳ ጽፎ በመጫን ተባበሩ:: ሰንጠረዡ ብዙ ገጽ ያለው በመሆኑ ከታች ያለውን የገጽ ቁጥር በመጫን መፈልግ ይቻላል አሊያም የሚፈልጉትን መዝሙር ርዕስ ሥaረቸሀ በሚለው ሳጥን ቢያስገቡ የተጣራ ውጤት ማግኘት ይችላሉ

እንዴት የመዝሙር ግጥም ላስገባ እችላለሁ?

በሰንጠረዙ 4ተኛ ክፍል ላይ የእርሳስ ምልክቱን ቁልፍ በመጫን ግጥሙን ለማስገባት የሚያስችል ዊንዶው ይመጣል:: ግጥሙ በጽሑፍ ካሎት ፔስት በማድረግና ሱበሚት የሚለውን ቁልፍ በመጫን ያስገቡ:: እዚሁ ግጥሙን መጻፍ ከፈለጉ ደግሞ ከሳጥኑ በላይ ያለውን ትንሽ ምልክት ሲጫኑ ለመጻፍ የሚያስችል ትልቅ ዊንዶ ይመጣል:: በእዚህ መሳሪያ በቀላሉ በመጻፍ ኮፒ ፔስት ማድረግ ወይም "OK" የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማስገባት ይችላሉ:: በመጨረሻ "Submit" የሚለውን ቁለፍ መጫን አይርሱ::

እንዴት የመዝሙር ዜማ ላስገባ እችላለሁ?

መዝሙሩን በስልኮ ወይም በኮምፒውተር ከቀዱ በኋላ መፕ፴ አድርገው ሴቭ ያድርጉት:: በሰንጠረዡ ፶ ተኛ ክፍል የሚገኘውን ቀስት ምልክት በመጫንና መዝሙሩን በመምረጥ "Upload" የሚለውን ቁልፍ በመጫን መጫን ይችላሉ

መፅሐፍ እንዴት ማስገባት እችላለሁ

መዝሙር መጻፊያና መጫኛመዝሙ ሮችን በስልክ ቀድቶ ለመላክ የሚከተለውን መንገድ ይጠቀሙ::
  1. መቅዳት የሚፈልጉትን ወይም የተመደቡትን የመዝሙር ዝርዝር ወይም ክፍል http://awdemehret.org/dashboard/ ወይም ከአውደ ምሕረት ሞባይል አፐልኬ ሽን ያውጡ
  2. ከዌብ ሳይቱ የእርሳስ ምልክቱን በመጫን ወይም ከሞባይል አፐልኬሽኑ የመዝሙሩን ርዕስ በመጫን የመዝሙሩን ስንኝ ማውጣት
  3. Mobile Application Pro dfsሰ የሚለውን ሞባይል አፐልኬሽን በመጠቀም መዝሙሮቹን በመቅዳት Google drive ላይ ያጠራቅሙ::
  4. መዝሙሮቹን በተሰጣቸው መለያ ኮድ መሰረት ለምሳሌ በመንፈስ የሐውር የሚለው መዝሙር መለያ ኮዱ 10 ስለሆን 10.mp3 በማለት ሴቭ ያድርጉ
  5. መዝሙሮቹን ሲቀዱ MP3 ፎርማት መሆኑን ያረጋግጡ:: በሌላ ፎርማት ከቀዱት ወደ MP3 ይለውጡት
  6. Mobile Application Pro ለመጠቀም የሚከተለውን ዮቲውብ ቪዲዮ ይከታተሉ
  7. በመጨረሻም የተቀዱትን መዝሙሮች ከ Google drive ወደ awdemehret1@gmail.com ኢሜል አካውንት ሼር በማድረግ መዝሙሩን መላክ ወይም አንድ በአንድ http://awdemehret.org/dashboard/ አፕሎድ የሚለውን አይከን በመጫን ወደ ሰርቨር መጫን ይችላሉ


ለትብብሮት በእግዚአብሔር ስም እናመሰግናለን