ደስ ይበለን ደስ ይበለን አምላክ አለ መሃላችን ምን ይከፈል ለዚህ ስራህ ገናና ነው አምላክ ክብርህ ምህረቱን አይተናልና አድርሶናል አምላክ በጤና ይህችን እድሜ የጨመረልን ለንስሀ ጊዜ የሰጠን ኃጢአትህን ይታገስሃል በቸርነት አምላክ ያይሃል ደስታ ነው በሰማያት በአንድ ኃጥእ የጽድቅ ሕይወት እልል በሉ የጎበኛሁ በምህረት አምላክ ያያችሁ በችግር ቀን ያሰበን ሁሉ አመስግኑት ዝምም አትበሉ ድንግል ማርያም ትጸልያለች ኃጥኡን ሰው ማረው እያለች በድንግል ክብር እንኖራለን በጽኑ ፍቅር አንድ እንዲያደርገን