ቃና ዘገሊላ/፪/ በዛ በሠርግ ቤት ተገኝተሻል ድንግል ከልጅሽ ጋራ ተገኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙበት ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት ድንግል እናታችን ቤዛዊት ዓለም አንቺ ደረሽለት ሆነሽው አማላጅ አዝ --- አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ አዝ --- የጌታ አምላክነት የተገለጸበት ምንኛ ታደለ የእነዶኪማስ ቤት ዛሬም ይኸው በዚህ በደብረ ምሕረት በረከት ፈሠሠ በአምላክ ቸርነት አዝ --- ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሲሆን በቃና ገሊላ ሁላችን አየን እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን ሁሉ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን