በመከራ ጽና በፈተና ጽና ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና ኢዮብ ተጨንቀ በጣም ተማረረ በመከራው ብዛት ትእግሥትን ተማረ ልጅ የሌለው ሆነ አጣ ንብረቱን በመከራ ጸና አልካደም አምላኩን በመከራ ጽና በፈተና ጽና ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና መፈተን መልካም ነው ያነጻል እንደወርቅ በመጨረሻው ቀን በክብረ እንድትደምቅ አንዱን ሳትሻገር ሌላው ቢተካብህ በሕይወትህ ዘመን ፈተና ቢያጠቃህ በመከራ ጽና በፈተና ጽና ለጊዜው ነው እንጂ ሁሉም ያልፋልና ከአምላክህ ተስማማ ራስህን አዋርድ በቃሉ ተመራ እንድፈቃዱ ሂድ ዋጋህ ከአምላክህ ዘንድ በሰማይ አለና በርታ ክርስቲያን ሆይ በፈተና ጽና