ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን እስከመቼ ድረስ ሕዝብህ ተጐሳቁሎ በረከሰ መንፈሰ ለርኩሰት ተጥሎ ምድር እያለቀሰች ደም እየሸተታት እባክህ አምላኬ ኢትዮጵያን ታረቃት እባክህ አምላኬ አገሬን ታረቃት ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን የዘመኑ ጣኦት ገንዘብ እያሳተን ይህ ደካማ ሥጋ አምላክን አስተወን ግብዝነት ሞልቶት ፈራሹ አካል በነፍስ በሽታ ሕዝባችን ታሟል/2/ ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን ክንፋችን ተመትቶ መብረር አቅቶናል በመንፈስ በሽታ ሕዝባችን ታዉኳል ምግባር የጐደለን ተራ ሰዉ ስለሆን እባክህ ጌታችን በፍጥነት ታረቀን /2/ ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን ጸጋህ የተለየን ባዶነት የመላን እርቅ የተነፈገን ሰላም የጐደለን ሆነን ስለቀረን እግዚአብሔር ታረቀን ጽድቅህን አድለን ጽድቅን ለተመኘን ቅያሜዉ ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን አንተ ስለራቅኸን ሞት ነዉ የከበበን