ኑ ተመልከቱልኝ የአምላክን ቸርነት አንደበት የለኝም ሥራዉን ለማዉራት ሰላምና ፍቅሩ በልቤ ተሞልአል በምን ቋንቋ ላዉራዉ ቃላቶች ያጥሩኛል /2/ ሰማይ ጉም ቢመስል ቀላያት ቢናጉ የጥፋት አጋንንት እጅጉን ቢተጉ እኔን የሚጠብቅ ኃይሉን አይሰዉርም እረኛዬ ከእኔ ዘወትር አይርቅም አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፍርሃት ከእኔ ላይ ጨለማም ተወገድ በጌታዬ ትምክህት እንደልቤ ልሂድ የሞት አበጋዞች ተስፋችሁ ጨልሟል እግዚቷብሔር ሊያድነኝ አጠገቤ ቆሟል አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ቅዱሳን በሙሉ ለእኔ ዘብ ቆመዋል ዉደእነርሱ ኅብረት ሊስቡኝ ጵጉተዋል ዘወትር በመዓልት ድንግል ትመጣለች በብርሃን እጆኟ ትባርከኛለች አዝ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥ ፥