ሰማየ በአብ ወበወልድ አርያመ ወበመንፈስ ቅዱስ ኀበ ዓረጉ አነ (2) ሰማዕኩ እመላእክት ዝማሬ በአድንኖ ወበአትሕቶ ቦ ዘያጽሕሱ ወቦ ዘይዜምሩ (2) ትርጉም :- በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስም ቸርነት ሰማይ ወጥኟ ጽርሐ አርያም ደርሼ ከመላእክት ዝማሬ (ምስጋና) ሰማሁ ከእነርሱም በዝቅ ና በትኅትና የሚያሸበሽቡ አሉ ዙሪያውንም ቆመው የሚዘምሩ አሉ