ሰዎች እንዘምር ለአምላካችን ከሞት ላወጣን ለአዳኛችን እናመስግነው እንደአቅማችን ምሕረት ለሠጠን ለሁላችን አምላክ ተአምሩን የሠራብህ ጩኸት ድምጽህን ለሰማልህ በርጠሜዎስ ሆይ አትተወው አዳኝ ጌታህን ተከተለው እውርነቴን ላስቀረልኝ ለዓይኔ ብርሃን የሠጠኝ ሁሌም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ አዳኜን ትቼ የትእሄዳለሁ አዝ --- በርጠሜዎስ ሆይ ታድለሃል የመዳን ጸጋ ተሠጥቶሀል እጹብ ድንቅ ነው የአምላክ ሥራ እውር የሆነው ዓይንህ በራ ይሄን ጌታዬን ምን ልበለው ለውለታውስ ምን ልክፈለው ስሙን ላወድስ ላመስግነው ለአምላክ ክፍያ ይህ ብቻ ነው አዝ --- ዓመት ደም ሲፈስሽ ሰዎች ሲንቁሽ ሲያንቋሸሹሽ ማን ፈወሠሽ አንቺ ሴት ያበቃሽ ማነው ለደኅነት እምነትሽ አዳነሽ አለኝና ኃይል ከእርሱ ወጣ የሚያጽናና የጌታ ልብሱን ብዳብሰው ደሜ ቀጥ አለ ላወድሰው በቤተ ሳይዳ በአልጋ ስትኖር በመጠመቂያው በወንዙ ዳር ደውይ ስትሆን በሽተኛ እንዴት ተፈወስክ አውጋን ለእኛ አልጋ ታቅፌ ስንገላታ መዳን ትሻለህ አለኝ ጌታ አምላኬ እርሱ ፈወሰኝ አልጋህን ይዘህ ሂድ አለኝ