እግዚአብሔር ሆይ ርዳን ቸርነት አድርገህ(2) ዕድሜ ለንሥሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ አላውቀውም ብሎ ሲጠየቅ ያመጸው ዶሮ እስኪጮህ ድረስ 3 ጊዜ የካደው የጅረት ወንዝ ነው የሰጠኸው እንባ ጴጥሮስ ተጸጽቶ ንስሐ እንዲገባ እግዚአብሔር ሆይ ርዳን ቸርነት አድርገህ(2) ዕድሜ ለንሥሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ ጽዋው እንዳይርደሰኝ የይሁዳ ዕድል ልጅህ ሆኖ ውሎ ኋላ መኮብለል ጴጥሮስ ዕድለኛው አልቅሶ ተማረ በትዕቢቱ ይሁዳ እንደወጣ ቀረ እግዚአብሔር ሆይ ርዳን ቸርነት አድርገህ(2) ዕድሜ ለንሥሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ ዘመኗን በሙሉ በዝሙት አቃጥላ ለንስሐ ጠራት ጌታ በገሊላ አልቅሳ ተማረች በእንባዋ ብዛት እግሩ ሥር ተደፍታ ማርያም እንተ ዕፍረት እግዚአብሔር ሆይ ርዳን ቸርነት አድርገህ(2) ዕድሜ ለንሥሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ ዐመጸኛው ልቤ ዛሬስ መች ይተኛል በኃጢአት በስርቆት በዝሙት ይዋኛል ወደ ቀድሞ ግብሩ እንዳይመለስ ፍቅርህ በእኔ ሠርፆ ኃጢአቴን ደምስስ እግዚአብሔር ሆይ ርዳን ቸርነት አድርገህ(2) ዕድሜ ለንሥሐ እንደ ሕዝቅያስ ሰጥተህ ጠማማውን ልቤን በቃልህ አቃንተህ በደላችንን ሁሉ ሳታስብ ትተህ በምጽአትህ ሰዓት ከጻድቃን ቆጥረህ ነጭ ልብስ ለብሰን ሆነን ከአንተ ጋራ በሩ ሳይዘጋ አስገባን አደራ