በክቡር ዙፋኑ መርጦ ያስቀመጠሽ ለእኛ ለኃጢአተኞች ተስፋቸን አንቺ ነሽ በፍጹም ትኅትና ቤተመቅደስ ያደግሽ የአማኑኤል የጌታዬ የፈጣሪዬ እናት በምን እንመስልሽ አዝ -------- ቃና ዘገሊላ ሠርግ ደግሠው አንቺን ከነልጅሽ በክብር ጠርተው ሰዎች ተረብሽው በጣም ተደናግጠው ወይኑ በማለቁ በፍርሃት ተውጠው አዝ ------ ወይኑ በመሀል ላይ ማለቁን ሰምተሸ ድንጋጤአቸውን እምቤቴ አይተሸ ወደ ልጅሽ ሄድሽ ብጠይቂላቸው ጋኑን ውኃ ሙሉ ብሎ አዘዛቸው አዝ ---------- የሚላችሁን አድርጉ ብለሽ ሰዎቹን ከሀፍረት ከጭንቀት ፈታሽ ድንግል እመቤቴ ቤዛዊተ ዓለም በመከራ ደራሽ እንደአንቺ የለም አዝ -------- ውኃውን ወደ ወይን አጣፍጦ ቀይሮ የዶኪማስንም እፍረቱን ሠውሮ እድምተኞች ሁሉ እስከሚደነቁ አምላክ ከእነርሡ ጋር መሆኑን አወቁ አዝ --------