ጥቅስ ማውጫ

ቁጥር ጥቅስ ምንባብ
11 መዝሙረ ዳዊት 50 : 1 - 1 አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
17 መዝሙረ ዳዊት 6 : 8 - 8 ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
7 መጽሐፈ ምሳሌ 18 : 13 - 13 ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።
16 ትንቢተ ሆሴዕ 14 : 1 - 1 እስራኤል ሆይ፥ በኃጢአትህ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።
2 ትንቢተ ሚልክያ 3 : 7 - 7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምር ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፡— የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።
8 ትንቢተ ኢሳይያስ 2 : 12 - 12 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል፤
13 ትንቢተ ኢሳይያስ 61 : 1 - 1 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
10 ትንቢተ ኤርምያስ 26 : 13 - 13 አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፥ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ክፉ ነገር ይተዋል።
5 ትንቢተ ኤርምያስ 31 : 34 - 34 እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፡— እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።
6 ትንቢተ ዮናስ 3 : 10 - 10 እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።
12 ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4 : 30 - 30 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
3 የሉቃስ ወንጌል 15 : 18 - 20 ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፡— አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ። ተነሥቶም ወደ አባቱ መጣ። እርሱም ገና ሩቅ ሳለ አባቱ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው።
19 የሐዋርያት ሥራ 17 : 30 - 30 እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤
15 የያዕቆብ መልእክት 4 : 17 - 17 እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።
9 የማቴዎስ ወንጌል 25 : 1 - 13 በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች። እርሱ ግን መልሶ፡— እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም፡ አለ። ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። እኩል ሌሊትም ሲሆን፡— እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። ሰነፎቹም ልባሞቹን፡— መ
14 የማቴዎስ ወንጌል 3 : 8 - 8 እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤