እሴብሕ ፀጋኪ ዘዘወትርእሴብሕ ፀጋኪ ዘዘወትር እሴብሕ ጸጋኪ ኦ እግዝእትየ ማርያም መላእክት ይሴብሑኪ በአርያም ወበምድር ደቂቀ አዳም ለዓለመ ዓለም አሜን። እሴብሕ ፀጋኪ ዘዘወትር እሴብሕ ጸጋኪ ኦ ምልእተ ጸጋ ወእትጋነይ ለኪ ኦ ምልዕተ ውዳሴ። ተዘከርኩ በሌሊት ንጽሐ ድንግልናኪ ዘኢማሰነ በፀኒስ ወኢረስሐ በሐሪስ እስመ ቅድስተ ቅዱሳን አንቲ ። ምልዕተ ጸጋ (ምልዕተ ክብር) እመቤታችን ሆይ የተሰጠሽን ጸጋ ክብር አመሰግናለሁ ምስጋናን የተመላሽ እምቤታችን በመውለድና አራስ በመሆን አደፍ ጉድፍ የሌለበት የድንግልናሽን ንጽሕና በሌሊት አስቤ ላንቺ እገዛለሁ፡፡ ከከበሩት ይልቅ አንቺ የከበርሽ ነሽና፡፡ እስመ ናሁ ይፈልሕ ሞገደ ፍቅርኪ በውስተ ልብየ በፄወ ክህነቱ ለበኵርኪ ቀስሚ ልስሐተ ልሳንየ። ምንት ረባሁ ለመሰንቆ ጽሩዕ ለእመ አልቦ ዘይሰነቅዎ ወምንተ ይደምፅ ንቃወ ሰንዚራ ዘስቁል ለእመ ኢተነፍሐ በድርገታተ ማኅሌት። የፍቅርሽ ማዕበል እነሆ በልቡናዬ ይፈላልና በልጅሽ ሥልጣን ጨው ያንደበቴን አልጫነት አጣፍጪው፡፡ የሚመታው ሰው ከሌለ የማይመታ መሰንቆ ጥቅሙ ምንድነው፡፡ በምስጋና አድነት ስልቱ ተለይቶ ካልተመታ የተሰቀለ በገና እንደምን ይጮሀል፡፡ በድኅንፃ መንፈስ ዝብጢ አውታረ መሰንቆሁ ለልብየ ወአስተንፍሲ ውስተ አፉየ ከመ እኩን እንዚራሁ ለበኵርኪ። ኦ ወለተ መርዓ ዘአልብኪ ሰብሳብ በዲበ ምድር ረስዪኒ እኵን ጽውዓ ውስተ ከብካብኪ ዘበሰማያት። የልቡናዬን መስንቆ አውታር በመንፈስ ቅዱስ በገና መምቻነት ምችው ለልጅሽም በገናው እሆን ዘንድ አንደበቱን አናግሪው፡፡ በዚህ ዓለም አደፍ ጉድፍ ነውር ነቀፋ የሌለብሽ የሠርግ ልጅ ሆይ በሰማይ ወደሚሆን ሠርግሽ እጠራ ዘንድ እንድጠራ አድርጊኝ፡፡ በነቀልቃለ ስብሐት ሁኪዮ ለአርጋኖነ ሕሊናየ ከመ ኢያርምም እምስብሐታተ ፍቅርኪ። ኦ መሥገርት ገሪፍ እንተ ተወደይኪ ውስተ ባሕረ ዓለም ወአስተጋብእኪ ኵሎሙ ዘመደ ዓሣት ዘውእቶሙ መሃይምናን አሥግርኒ በሐብለ ወንጌሉ ለበኵርኪ። ከፍቅርሽ ምስጋና ዝም እንዳልል የልቡናዬን በገና በምስገና መነዋወጥ አነዋውጪው፡፡ እነዚህም ምእመናን ናቸው የዓሣን ወገኖች ሁሉ ሰብስበሽ የያዝሽ በዚህ ዓለም ባሕር የተጣልሽ መረብ እመቤታችን ሆይ እኔንም በልጅሽ በወንጌሉ ገመድ እንድያዝ አድርጊኝ ማለት እንድያዝ አድርጊኝ፡፡ እስመ ናሁ እጸብት ውስተ ባሕረ ኃጢአት አውጽእኒ እምሠርመ አበሳ ወጌጋይ ወአስጥምኒ ውስተ ቀላየ ምሕረቱ ለበኵርኪ። ሚጢ ላህየ ወአስተፍሥሕኒ ስጥጢ ሠቅየ ወሐሤተ አቅንትኒ። እነሆ በኃጢአት ባሕር እዋኛለሁና በኃጢአትና ከበደል ረግረግ አውጥተሽ በልጅሽ በይቅርታው ጥልቅ ባሕር እንድሠጠም አድርጊኝ፡፡ ልቅሶዬን ወደ ደስታ መልሰሽ ደስ አሰኚኝ፡፡ ይኃዘን ማቴን ቀደሽ በደስታ ዝናር አስታጠቂኝ፡፡ አዕትቲ ፄዓተ ኃጣውእየ በመዓዛ ዕፍረትኪ መዝምዝኒ አንጽሒ ርስሐትየ በደመ ወልድኪ ቅድስኒ፡፡ አድኀንኒ እማዕገተ ጸላኢ ወባልሀኒ እመሥገርተ ከናፍር ወልሳን ወእምትንሣኤ ፀር ዘኀቡዕ ወዘገሃድ ፡፡ የኃጢአቴን ክፍ ሽታ አርቀሽ በሽቱሽ መዓዛ እሺኝ ከኃጢአቴ አንጽተሽ በልጅሽ ደም አክብሪኝ፡፡ ከጠላት መክበብ ካንደበትና ከከንፈር ወጥመድ ጠብቀሽ ተገልጾና ተሠውሮ ከሚነሣ ጠላት ማለት ከወዳጅ ጠላት አድኚኝ፡፡ ዕቀብኒ በሐራ ወልድኪ ልቡሳነ ብርሃን ከመ ኢይቅረቡ ኀቤየ ሠራዊተ መስቴማ ጽልሙታን። መልከቸው ጨለማ የሆነ የዲያብሎስ ሠራዊት ወደኔ እንዳይቀርቡ ልብሳቸው ብርሃን በሚሆን በልጅሽ ጭፍሮች መላእክት ጠብቂኝ፡፡ አንሰ ገደፍኩ ነፍስየ ወሥጋየ ውስተ እዴኪ ወእትማኀፀን ብኪ ከመ ታድኅንኒ በዝ ዓለም እምእደ ሰብእ እኩያን ወበዘይመጽእ ዓለም እምእደ ሰይጣን ወእም አጋንንቲሁ ፀዋጋን እለ ይሰክዩ ነፍሰ ወይስሕቡ ውስተ አንቀጸ ደይን። ነፍሴንም ሥጋዬንም በእጅሽ ጥዬ ባንቺ እማጠናለሁ፡፡ በዚህ ዓለም ከክፋ ሰዎች እጅ በሚመጣውም ዓለም ከዲያብሎስ እጅ ነፍስንም እያከሰሱ ወደ ሲኦል ደጃፍ የሚያደርሱ ክፋ ከሚሆኑ ከአጋንንትም ታድኚኝ ዘንድ ፡ ስፍሒ እዴኪ ወባርክኒ ለገብርኪ በረከተ ዚአኪ የሃሉ ወጸጋ ወልድኪ ላዕለ ኵልነ ካህናተ ቤትኪ አግብርትኪ ወአዕማትኪ ለዓለመ ዓለም አሜን። እጅሽን ዘርግተሽ እኔን ባርያሽን ባርኪኝ፡፡ ያንቺ በረከት የልጅሽም ቸርነት በኛ በወንዶችም በሴቶችም ባሮችሽ ላይ ለዘለዓለሙ ይኑር በእውነት ያለ ሐሰት፡፡ |