የምህላ ጸሎትየምህላ ጸሎት አብ ሆይ ማረን ሃሌ ሉያ ወልድ ሆይ ይቅር በለን ፤ ሃሌ ሉያ ፣ ይቅር ባይ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በይቅርታህ አስበን (3 ጊዜ በል) ለአንተ ፍጹም ምስጋናን እናቀርባለን። ቸር ይቅር ባይ ሆይ ማረን፤ ኃጢአታችንንም አስተሥርይልን፤ የእግዚኣብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አድነን በነፍስ በሥጋም ጠብቀን ። አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅር በለን ። በቸርነትህ ብዛት በደላችንን ደምስስ ፤ ይቅርታህንም ላክልን ። ይቅርታ ካንተ ዘንድ ነውና ፤ ሃሌ ሉያ ይቅር ባይ አብ ሆይ ማረን ። ይቅር በለን መሐሪ የሆንህ አቤቱ ይቅርታህን ስጠን ! የቀድሞ ኃጢአታችንንም አስባህ አታጥፋን ። በቸርነትህ አንተ ይቅር ባይ ነህና ፤ ለሚጠሩህ ለሚለምኑህ ሁሉ ይቅርታህ ብዙ ነው ። በእውነት ይጠሩሃል ፤ አንተም ዘወትር ትሰማለህ ፤ ሁሉን ለማድረግ የምትችል ነህ ሁሉን ለማድረግ የሚችል የአምላካችን ቃሉ እውነት ነውና ። ይቅርታውን ይልክልን ዘንድ አብን እንለምነው ፤ አብ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና ሃሌ ሉያ ለርሱ ምስጋና ይገባል ሃሌ ሉያ ለርሱ ክብር ምስጋና ይገባል ። ሃሌ ሉያ ለሁሉ ጌታ ለክርስቶስ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ። ዛሬስ ተስፋዬ ማነው እግዚኣብሔር አይደለምን ? አቤቱ ነፍሴን ላንተ አደራ አስጠብቃለሁ ከምሕረት አምላክ ዘንድ ነፍሴን አደራ አስጠብቃለሁ፤ ከምስጋና አምላክ ዘንድ ነፍሴን አደራ አስጠብቃለሁ ። በጌታዬና በአምላኬ ነፍሴን አደራ አስጠብቃለሁ ከክፉ ሥራ ሁሉ ሰውነቴን(ነፍሴን ) አድናት ። ኑ እንለምነው እንለምነው እንማልደው የአምላካችን ቃሉ እውነት ነውና ። ሁሉን የሚችል የሚሳነውም የሌለ እርሱ ነው የድሆች አምላክ ተስፋ ላጡ ተስፋቸው የምትሆን አቤቱ! እኛ ወዳንተ ተማጥነናል (3 ጊዜ በል) |
ከጧት እስከ ማታ እንደጠበቅኸን አቤቱ እንዲሁ ከማታ እስከ ጧት ጠብቀን (3 ጊዜ በል) እኛን ወገኖችህን አድነን ፣ የጥንት ተገዥዎችህንም ባርከን ፣ ስምህን ለምንጠራ ለኛ ለአገልጋዮችህ ድል መንሳትንና ኃይልን ስጠን ። የወገኖችህን ልጆች እኛን ጠብቀን በየጊዜውና በየሰዓቱ በመላእክት ታዳጊነት በውስጥ በአፍአ ጠብቀን ። በመስቀልህ ታዳጊነት እርዳን ። በመስቀልህ ተቤዤን ። ስለ ባለሟልህ ስለ አብርሃም ፤ ስለ ወዳጅህ ስለ ይስሐቅ ፣ ስለ መረጥከው ስለ እስራኤልም ብለህ አቤቱ ቃል ኪዳንህን አስብ ይቅርታህን ፈጥነህ ላክ የፈጠርኸን እኛን ማረን ። የወገኖችህንም ኃጢአት አስተሥርይ ፤ የእጅህን ፍጥረቶች እኛን ማረን ፤ አቤቱ አታጥፋን ፤ ይህ በአንተ ዘንድ አይደረግ በእናትህ በማርያም አማላጅነት ፣ በአጥማቂህ በዮሐንስና በቅዱሳንህም ሁሉ አማላጅነት ሁል ጊዜ በመስቀልህ ታዳጊነት እርዳን፤ አቤቱ በፊትህ አታሳፍረን። እመቤታችን ሆይ ወደኛ ተመልከቺ ፤ ለኛ ለልጆችሽ ለምኚልን ፤ ከችግርና ከኀዘን ሁሉ አድኝን ። አቤቱ ጌታችን ሆይ ቀን ከኛጋር ሌሊትም በመካከላችን ሁን አቤቱ አንተ ከኛ አትለይ ከኛ ጋራ ኑር፤ ረዳትም ሁነን ፣ አትተወን አትናቀንም የሰላም አምላክ ሆይ ተራዳን። (3 ጊዜ በል) እመቤታችን ሆይ እመቤታችን ሆይ ወደኛ ተመልከቺ ፤ የልጅሽም ሰላም በኛ ላይ አድሮ ይኑር ( 3 ጊዜ በል ) አቤቱ ክርስቶስ ማረን ። (3 ጊዜ በል) |
የቤተ ክርስቲያን ጸሎት። አቤቱ ፈጣሪያችን ሆይ ፍቅርን አንድነትን ስጠን። አቤቱ ፈጣሪያችን ሆይ ፍቅርን አንድነትን ስጠን ። ንጉሣችን ክርስቶስ ሆይ ወንድሞቻችንን ይቅር በላቸው እኛንም ይቅር በለን ። ትእ. ከዚህ በኋላ የኪዳን ጸሎት ቅዱስ ተብሎ ለማታ ጸሎት የተሠሩት 3ቱ ኪዳናት ይባሉ ። ሕዝቡም ቆመው ይስሙ ተሠጥዎውንም ይቀበሉ ። ትእ. ከኪዳን በኋላ ሕዝቡ እንደቆመ የምህላውን ጸሎት በግራና በቀኝ ይበሉት። ትእ. ከዚህ በኋላ ሕዝቡ እንደቆሙ ጸሎተ ሃይማኖትን ይድገሙ ትእ. ጸሎተ ሃይማኖት ከተደገመ በኋላ ሕዝቡ ይቀመጡ ። ቁሱ በክርስቶስ ፍቅር ስለመጽናት ያለውን ቃለ ስብከት ወይም ሌላውን ስብከት ያስማቸው፤ |