colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

መልክአ ጊዮርጊስ

፩፤ ለፅንሰትከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስከው መፀነስህና በወርኃ ታኅሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ስለዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደ ገበረ እኔም ፍጹም ልባዊ የሆነ እጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ፡፡ ፪፤ለተኃፅኖትከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለአደግኸው አስተዳደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በጠንካራው የጽድቅ ክንድህ ደግፈህ ያዘኝ፡፡ እጅግ ጥልቅ የሆነ የፍትወተ ሥጋ ጉድጓድ ልትጨምረኝ ዓለም በፊቴ ወጥመዷን አጥምዳለችና፡፡ ፫፤ለዝክረ ስምከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በዕንጨት ያይደለ የብርሃኑ ጸዳል እጅግ በሚያበራ ዓምደ ብርሃን ለተቀረፀ ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በኃጢያት ድጥ ላይ ለመውደቅ የሚፍገመግሙትን በኃይል ክንድህ ፈጥነህ የምትደግፍ ነህና በዓለም ላይ መልካም ዝናን ለአተረፈው ስም አጠራርህ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፤ ግብፅም ትዘምራለች፡፡ ፬፤ ለስርእተ ርእስከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በቅብዐ ሃይማኖት ለለሠለሰ ስእርተ ርእስህና በጠፈረ ክሣድህ ላይ ለሚገኘው ርእስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በትሩፋተ ገድል በዋጀኃት በመንግሥተ ሰማይ ክፍልህ በዚያ ከኔ ጋር ይሁን ስትል በጆሮዬ ንገረኝ፡፡ ፭፤ ለገጽከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በመዓልት ላይ ሠልጥኖ ከሚያበራ ፀሐይ ይልቅ ሰባት እጅ ለሚያበራው ሥነ ገጽህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ምጽዋትን እንደዘር የምትዘራ ለጋስ ባለጸጋ ንህና ሙሽራው ድንገት ሌሊት በመጣ ጊዜ ከአንተ ጋር መብራት አብርቼ እቀበለው ዘንድ ከትሩፋተ ገድልህ የመብራት ዘይት አካፍለህ ስጠኝ፡፡ ፮፤ ለቀራንብቲከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በባለሟልነት ጸጋና ግርማ ሞገስ ለተሸለሙ ቀራንብቶችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ለሥጋዊ መድረክ መብራት ለሆኗት ዓይኖችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በተከበሩት ጉባዔ መካከል አንተ እጅግ የተከበርክ ነህና የአእምሮህን ሕግ በልቡናዬ ሠሌዳ ላይ ጻፍ፡፡ አእምሮየ ትክክል ያይደለ ነውና፡፡ ፯፤ ለአዕዛኒከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በኅዘን ላይ ያለውን ሰው ጸሎትና በትካዜ ላይ የምትገኘውን ሴት የልመና ቃል በቅጽበት ለሚሰሙ አእዛኖችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ልዩ ልዩ ተአምራትህን ከማድረግህ ጋራ መሐሪ እንደ መሆንህ ሁሉ ሁሉን የምትረዳ የተለያዩ ስጦታን የምትሰጥ ስትሆን በኔ ዘንድ ልቦናህ ስለምን ይጨክናል፡፡ ፰፤ ለመላትሒከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ኃጥኡን ሰው ለማዳን ከሱ ዘንድ የንስሐ ዕንባ ምንጭ ለሚፈልቅበት ጉንጮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ጽኑዓን መሰናክሎችን በአሸናፊነት ለመወጣት ልዩ ኃይል ነህና አቤቱ ከሥውር የሰይጣን ወጥመድ ሠውረኝ ከግፈኛ ሰው መገፋትም አድነኝ፡፡ ፱፤ ለአእናፊከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከወርቅ ከዕንቁ ይልቅ ንጽሐ ድንግልናዋ የሚያንጸባርቀው የድንግል ማርያምን ንጽሐ ድንግልና ገና በሩቁ ለሚያሸትቱ አዕናፎችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ አነዋወርህ ሉዓላዊ ምጡቅ እንደመሆኑ መጠን የመብረቅን ሠረገላ በፊትህ በማስቀደም የዚያን የውዳቂ ጋኔን ሠራዊት ጠላቶቼን ተከታትለህ አጥፋቸው፡፡ ፲፤ ለከናፍሪከ ወላአፉከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከሥነ ስርዓት ውጭ ላለመናገር ተጠብቆ ለመኖር ሕግን ለአቋቋሙ ከናፍርህና አፍህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ምግባረ ሠናይን አጠናቀህ የያዝህ ፍጹም መነኮስ አንተ ያለ እህል ውሀ ተጋድሎህን ስታካሂድ ተመልክታ የነበርክባት ገዳም ወይም ጭው ያለችው በረሃ ትዕግሥትን ፈጽማ አደነቀች፡፡ ፲፩፤ ለአስናኒከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በኃጢያት መጥረስ ላልጠረሱ አስናኖችህ ሰላም እላለሁ፡፡ የምድራዊ መብልን አጣጥሞ ከማላመጥ ፈጽመው የተወገዱ ናቸውና፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ግሩማን አናብስትን በሥልጣንህ ሥር አውለህ የምትገዛ ነህና፡፡ አንተን የምትወድ በደዌ ኃጢአት ለምትሠቃይ ሰውነቴ ብልሁ ቀሲስ ሆይ፤ መድኃኒቷን ፈልግላት፡፡ ፲፪፤ ለልሳንከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ዕውነተኛውን የክርስቶስን ሃይማኖት ላስተማረ አንደበትህና ችግርን ለሚያቃልል ሥልጣነ ቃልህም ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ መንግሥተ ሰማያት ላንተ ፈጽማ የተዘጋጀች ናት በጠላት ዲያብሎስ ዘንድ እንደ ዕባብ ብልህ ስትሆንበት በቅዱሳኖች በኩል ልክ እንደርግብ የዋህ ሆነህ ተገኝተሃልና፡፡ ፲፫፤ ለእስትንፋስከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ሕሙማንን በልብሱ ዘርፍ ፈውስ የሚሰጥ አንደበቱ ከመዓር ከወተት የሚጣፍጥ በአምላኩ ኃይል አዳኝ ከሚሆን ከጳውሎስ እስትንፋስ የማዳኑ ተባባሪ ለሚሆን እስትንፋስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ የኢየሱስ ክርስቶስና የባሕርይ ሕይወቱ የሚሆን የመንፈስ ቅዱስ ታማኝ አገልጋይ ነህና፡፡ ከዚህ ዓለም ኃጢአት ንጹሕ ያደርገኝ ዘንድ የእስትንፋስህ ተን ከእስትንፋሴ ጋር አንድነትን ይፍጠሩ፡፡ ፲፬፤ ለጕርዔከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ የውሃን መጠጥ እስከመናቅ ድረስ ከማንኛውም ምግብ ለተገለለ ጕርዔህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ረዳትነትህንና የታመነ ቃል ኪዳንህን የተመለከቱ ሁሉ አባት ሆይ፤ የቃል ኪዳንህ ዓሥራት አድርገን እያሉ ይማልዱሃል፡፡ ፲፭፤ ለክሣድከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በሐሰተኛው በዚህ ዓለም ጌጥ ያይደለ በአምላክ ባለሟልነት ለተሸለመ ወይም ለተጌጠ ክሣድህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በገጸ ሃይማኖት ሰማይ የተሠየምክ ደመና እንደመሆንህ የቸርነትህ ዝናም በሚያስፈልገው ቦታ ዘንማ የሰውነቴን በረሃነት ወደለምለምነት ለወጠችው እኮን፡፡ ፲፮፤ ለመትከፍትከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከባዱን ፃማ ድካም በመቀበል የቅዱሳንን አርዑተ ምንኩስናንን ወይም የምንኲስናን ቀምበር ለተሸከመ ትክሻህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በተፈጥሮዋ መጠን አነስተኛ የሆነች እንደ ንህብ የጽድቅህ ሥራ በአዲስ የዜማ ስልት ሲዘመር የጣዕሙ ፍሬ መላእክትን ደስ ያሰኛል፡፡ ፲፯፤ ለዘባንከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ እራቁትንና ቊርን ለመቋቋም በሣር ምሳሌ ፀጉር ለአበቀለ ዘባንህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በምድር ላይ ከሚገኝ ጌጣ ጌጥ ሁሉ የተወገድህ ነህ እኮን፡፡ ስለዚህም የአባታችን የአባ ዮሐንስ ሐፂር የፍቅርና የትኅትና ሥርዓት በአንተ ላይ ተፈፀመ፡፡ ፲፰፤ ለእንግድዓከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ዕውቀትና ጥበብን በማስገኘት ከሕፅንህ ጋር ትክክል ለሚሆን እንግድዓህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ከፍትወታት ኃጣውእ ተጋዳዮች አባቶች አንተ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለህ በነፋስ ክንፍ ተጭነህ ትበራለህና ደመናም የጫማህ መረገጫ ነውና፡፡ ፲፱፤ ለአዕዳዊከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ክርስቶስን የምስጋና መሥዋዕተ ቁርባን ለዳሠሡ ለአንተ ለካህኑ እጆች ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ከተከበረው ወገን የተገኘ ቀሲስና ከተባረከው ዘር የተገኘ ዲያቆን አሜን አሜን እያልኩ በአንተ እጅ ንጹህ ቁርባንን መቀበል ማን በከፈለኝ፡፡ ፳፤ ለመዛርዒከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ፈጽመው ለማይለያዩና ለማይነጣጠሉ ኵርናዕህና መዝራዕትህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ የልዑል እግዚአብሔር ዐቃቤ ሕግ አዋቂ ብልህ ነህና ሕንፃውና ምርጉ ከፈረሰ ዘንድ የነፍሴን አዳራሽ በቅድስና ጌጥ አስጊጠህ አሳድስልኝ፡፡ ፳፩፤ ለብፁዓት እመታቲከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከብፁዓት መዳፎችህ ጋር በማስተባበር ለተመሰገኑ ክናዶችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በጧት ገሥግሠው ከመጡት ሠራተኞች ይልቅ እኔ ከረፈደ በኋላ በሠራ ቦታህ ተቀጥሬ ለምሠራ አገልጋይህ በአንተ ዘንድ ሳታውል ሳታሳድር ዋጋዬን በቅድሚያ ለመስጠት ስጦታህን አስቀድም፡፡ ፳፪፤ ለአጻብዒከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በጸሎት ጊዜ እንደ ፋና መብራት ለሚያበሩ ጣቶችህና አጽፋሮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ለተናቀ ሥጋዊ ፈቃድ ንብረቴን ብበትንና ባጠፋ አባት ሆይ፤ አንተ በቸርነትህ ብዛት እኔን ጎስቋላውን ልጅህን ተቀበለኝ፡፡ ፳፫፤ ለገቦከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ምንጣፍን ለማይፈልግ በአክናፍ ለተሸለሙ ጎንህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ስምህ በሰማያዊ ዓምደ ወርቅ የተጻፈ ነውና፤ የሰማይ መላእክት እያዩ ዘወትር ያነቡት ዘንድ ተገድፎ እንዳይቀር የኔንም ስም ከአንተ ስም ጋር በዚያ ጻፍልኝ፡፡ ፳፬፤ ለከርሥከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ስንፍናን የሚያመጣ ምድራዊ ኅብስት ያይደለ ሰማያዊ ኅብስትን ለተመገበ ከርሥህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ሁሉ በግልጽ ያከብርሃል፤ ሁሉም ያደንቅሃል፤ ለዕውራኖች ብርሃናቸው ለሐንካሶች ምርኩዛቸው፤ ለማይሰሙትም የመስሚያ ቃለ ድኅንፃቸው ሆነሃልና፡፡ ፳፭፤ ለልብከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከቂም በቀል ለራቀ ልቡናህ ሰላም እላለሁ፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የጥበቡ ብርሃን በሱ ዘንድ አንጸባርቋልና፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ለጠላቴ መሳቂያና መሣለቂያ እንዳልሆን ጽድቅን የሚያስገኝ የትሠህትናን ሕግ አስተምረኝ፡፡ ትዕቢት ሰይጣንን ከውርደት ላይ የጣለ ነውና፡፡ ፳፮፤ ለኵልያቲከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከቀድሞው የኦሪት የፋሲካ በዓል ከበግና ከፍየል ኵልያት ከሚቀርበው መሥዋዕት ይልቅ ለተቀደሱትና ለተባረኩት ኵልያቶችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ብርሃንን የተጎናጸፍክ እንደመሆንህ መጠን ምድራዊ አዳራሾችን ሕንፃዋ ከፈረሰ መሠረቷ ከነዋወጸ ዘንድ በሰማያዊት ሀገር መሠረቷን አጽንተህ ግብረ ሕንፃዋን አሣምር፡፡ ፳፯፤ለኅሊናከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ነውር ነቀፋ ለሌለበት ኅሊናህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ የባለ ዓሥር ሺህ መክሊተ ወርቅ ባለቤት ትጉህ መንፈሳዊ ነጋዴ ነህና የጌታውን ወርቅ በምድር የቀበረ በዚያ በሰነፉ አገልጋይ የተመሰልኩ እኔን አገልጋይህን ጌታህ በሾመህ ቦታ ከኋላህ አስከትለኸኝ ተጓዝ፡፡ ፳፰፤ለአማዑቲከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ እንደዚህ ዓለም ንብረት በገንዘብ ተገዝቶ ለማይገኝ ውስጣዊ ሰውነትህና አማዑትህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ መዓዛው ጣፋጭ የሆነ መልካም ሽቱ ነህና የአንተ ጼና መዓዛ በሚሸትበት አካባቢ ሁሉ ሌላው ሽቱ ዋጋ የሌለው ከንቱ ነው፡፡ ፳፱፤ ለኅንብርትከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከእግር እስከ እራስህ ባሉት ሕዋሳቶች መካከል በሚገኝ በሰሌዳ ከርሥህ ላይ ለተቀመጠ ሕንብርትህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ወደአንተ አጥብቀው የሚለምኑ የምድር ነዳያን ሁሉ ብልጽግናን ያግኙ፡፡ የተራቡትም በእህል በረከት ይጥገቡ፡፡ ፴፤ ለሐቌከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ከመከራና ከሕማም ሐብል እንዲሁም ግዙፍ ከፀጉር ሠቅ በስተቀር የቆዳ ሠቅ ላልታጠቀ ወገብህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ አማልደህ ሰላምን የምታሰጥ ታላቅ መምህር ነህና፡፡ አባት ሆይ፤ መልካሙን ጠባይና ጣፋጩን የአነጋገር ሥነ ምግባር አስተምረኝ፡፡ ፴፩፤ ለአቍያጺከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ለመቅደስ ሰውነትህ ዓምድ ለሆነው አቍያጽህና ስግደት የዘወትር ግብራቸው ለሆነ አብራኮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ስለእመቤታችን ማርያምና ስለተወደደው ልጅዋም ብለህ ከዚያ እጅግ ከሚያስፈራና ከሚያስጨንቅ ሰዓት ነፍሴን ሰውነቴን አድናት፡፡ ፴፪፤ ለአዕጋሪከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ መመሪያ ጥበቧ የዕብደት የሆነ በዚህች ዓለም ጎዳና ላልተጓዙ እግሮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ሐዋርያዋ አንተ ነህ እኮን፡፡ በአውራጃዋ ሁሉ ዜና ትሩፋትህ ተሠራጭቷልና እስከ ምድርም ዳርቻ ሁሉ ትምህርተ ሃይማኖትህ ተዳርሷልና፡፡ ፴፫፤ ለሰኮናከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ የአዳምን ሰኮና ያቆሠለ የዕባብ ዲያብሎስ የተንኮሉ መርዝ ሊቀርበው ላልቻለው ሰኮናህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ክርስቶስ ካለበት በዚያ ትኖር ዘንድ የጳውሎስን ቃል አስበህ የክርስቶስን መስቀል ተሸክመህ ከሀገር ወጣህ፡፡ ፴፬፤ ለመከየድከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በጫማ ፋንታ ሥውር የሆነች ፍለጋዋ የማይገኝ የጸሎትን ሠረገላ ለተጫሙ መከየድህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ እኔ የማርያም ታማኝ አገልጋይዋ የሆንኩት የምስጋና ደብዳቤ ያነቡልኝ ዘንድ ለሰማያውያን መላእክት አስታውሰህ ንገርልኝ፡፡ ፴፭፤ ለአጻብዒከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ለእግር ጣቶችህና በግራ በቀኝ ለሚገኙ ዓሥሩ አጽፋሮችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ እግዚአብሔርን ደስ ወደማሰኘት ፊቴን እስክመልስ ድረስ ፈጥኖ እንዳይጠራኝ አምላክህን ማልድልኝ ለምንልኝ፡፡ እሱ ምሕረቱ የበዛ ፍጹም ታጋሽ ነውና፡፡ ፴፮፤ ለቆምከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ገና መጠኑን ሳያደርስ አባትህ ዘመደ ብርሃንን እንደ መልአክ ቁመና ለአስደነቀው አካለ ቆምህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ በፈጣሪ ክርስቶስ ፊት ቆሞ ሰማዕት ደሙን፤ ጻድቅም ጾሙን በሚያሳስብበት ጊዜ ከዚያች ከቂምና ከበቀል ሰዓት ሠውረኝ፡፡ ፴፯፤ ለመልክእከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ደም ግባቱ ለሚያንጸባርቅ ሥነ መልክእህ ሰላም እላለሁ፡፡ ቅብዐ መንፈስ ቅዱስን ተቀብቷልና፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ አንተ ምድራዊ ስትሆን፤ ሰማይን ትገዛለህና ስለዚህ ነገር አንደበቴ ምስጋናህን ይናገራል በፍጹም ልቡናየም ለአንተ እገዛልሃለሁ፡፡ ፴፰፤ ለፀዓተ ነፍስከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ አነዋወሯ የሞተ ድምፅ ከማይሰማበት የሕማም ዜና የማይነገርበት ቦታ ለሚሆን ፀዓተ ነፍስህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ የገዳማውያን መነኮሳት አለቃቸው እንደ መሆንህ በብርሃናት ፀዳል የተሸለሙ መላእክት ሙሽራው አንተን ይቀበሉ ዘንድ ከላይ ከሰማይ ወረዱ፡፡ ፴፱፤ ለበድነ ሥጋከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ያዕቆብና ዮሴፍ ወደሱ ለመቅረብ እስኪፈሩ ድረስ በሰማይ ብርሃን ለተከበበው በድነ ሥጋህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ይህን መንፈሳዊ ብልጽግናህን የሚያቃልል ቢኖር ኃይለኛ ጉልበተኛ ሹመቱን ይቀማው፤ ባለዕዳም ቤቱን ንብረቱን ይበርብረው፡፡ ፵፤ ለግንዘተ ሥጋከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ክብር ምስጋና ለተገባው ለግንዘተ ሥጋህ ሰላም እላለሁ፡፡ መጽሐፈ ገድልህ ግን ስለሁኔታው አይገልጽም፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ለኔ ግን ግንዘተ ሥጋህ በመላእክት እጅ ይመስለኛል፡፡ ዳሩ ግን እሱ እግዚአብሔር ብቻውን ቢያውቅ እንጂ ሌላ ማን ሊያውቅ ይችላል፡፡ ፵፩፤ ለመቃብሪከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ እንደ ዮካብድ ልጅ እንደሙሴ መቃብር አድራሻው ላልታወቀና ለማንም ላልተገለጸ መካነ መቃብርህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ነገር ግን መቃብርህ በኢየሩሳሌም ነው የሚሉ አሉ፡፡ በምድረ ከብድም ነው የሚሉ አሉ፡፡ ፵፪፤ ዝውእቱ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ የምስጋና ምስጋናንም የመቀበል ሰዓቱ አሁን ነው የመልክእህን ድርሰት በየክፍሉ በሚቻለኝ ጀምሬ ከፍጻሜ አድርሻለሁና፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ የተሠወሩ ወይም የተገደፉ ቃላቶች ቢኖሩ ግን ከዚህ ውስጥ የጎደለ ወይም የተጨመረ ነገር የለም እንዲያው ሁሉ በሁሉ ምሉዕ የሆነ መልካም ነው እንጂ በለኝ፡፡ ፵፫፤ ለሞገሰ ስምከ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ በአምላክ ትእዛዝ ለተሰየመ የባለሟልነት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ክብርህ ከመላእክት ክብር ያላነሰ ነው እኮን፡፡ ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ አባቴ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ፤ ሰውነቴ በአንተ ፍቅር ተፀምዳለችና አንደበቴን ግለጥ ልቦናየንም አብራ፡፡ ፵፬፤ ለአፃብዒከ ጽዱላት፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ ዘወትር እንደ መብራት ለሚያበሩ ጣቶችህ ሰላም እላለሁ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ አንደበትህ እንደጳውሎስ አንደበት የጣፈጠ ነውና ሄኖክ ከሞት በፊት እንደ ተሠወረ እኔንም የመቅሰፍት ዘመን እስኪአልፍ ድረስ በጸሎትህ ሠውረኝ፡፡ ፵፭፤ ሃምስተ ምዕተ፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ፤ አምስት መቶ ስሳ ሁለት ዘመን በገዳም ስትቀመጥ እግዚአብሔር በጸጋ የሰጠህ በመላ አካልህ የበቀለው ጸጉር ልብስ ሆኖህ ኖርህ፡፡ ክቡሩ አባት ሆይ፤ ሥጋዊና መንፈሳዊ ጥበብን ግለጽልኝ፡፡ ይልቁንም የጸሎትህ ኃይለ ቃል ረዳቴ በመሆን ዓሥራት በኩራት አድርጎ ይጠብቀኝ፡፡ ፵፮፤ ስምዖን ወአቅሌስያ፡፡ ንኂሳ በሚባል አገር የሚኖሩ ስምዖንና አቅሌያስ የተባሉ ልጅ በማጣታቸው ለሠላሳ ዓመታት ያህል ሲያዝኑ ሲኖሩ፡፡ ሥሉስ ቅዱስ በአቅሌያስ ማኅፀን ሀብተ ጸጋን ቢያሳድሩ በአምላኩ ኃይል አናብስትን የሚገዛ ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ተወለደ እግዚአብሔር ያሳትፈን ከትሩፋቱና ከክብሩ፡፡ ፵፯፤ ክብሩ አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ በቀላል ኪዳኑ በዘባነ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ የታዘለ ሦስት ገጽ አንድ አምላክ ብሎ ያስተማረ የትምህርቱ ሥነ ጸዳል ፈጽሞ የአበራ ሥጋዊ ሥርዓተ ቀብሩም በኢትዮጵያ የተፈፀመ እሱ ንዑድ ክቡር ነው፡፡ ፵፰፤ አቤቱ የብፁዕ አባታችን የገብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ሆይ፤ ስለክብሩ ጻድቅ ብለህ ከመከራው ሁሉ እኔን አገልጋይህን ሠውረኝ ለጠላትም አሳልፈህ አትስጠኝ ጠብቀኝ እንጂ አትተወኝ እኔ የአንተ ፍጥረት አንተም የኔ ፈጣሪ ነህና ክብር ምስጋና ለአንተ ይገባል ለዘላለሙ አሜን፡፡