colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

መልክዐ ውዳሴ ዘሰንበት

ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ማርያም እምነ ናስተበቍዓኪ። እምዓርዌ ነአዊ ተማኅፀነ ብኪ በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።

እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን ፤ እንማልድሻለን። ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል። ስለ እናትሽ ፣ ስለሐና ብለሽ ፤ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄ ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።

ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት አምአኑስ አንቲ ውእቱ ቀመረ መድኃኒት ሐዳስ። ማርያም ድንግል ወለተ ዳዊት ንጉሥ ሰላም ሰላም ለመልክዕኪ ውዱስ ለለ፩ዱ እስከ እግር ወርእስ።

በሰዎች ሁሉ የተወደድሽ ፤ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አዲስ አማናዊቱ (እውነተኛይቱ) ቀመር አንቺ ነሽ። የንጉሥ ዳዊት ልጅ ድንግል ማርያም ከእግር እስከ ራስ ለእያንዳንዱ ፤ ለተመሰገነው መልክሽ ሰላም ሰላም እላለሁ።

ታቦት አንቲ ዘረሰየኪ ታዕካሁ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ ሥጋኪ ሥጋሁ። ማርያም ድንግል ለእጓለ እመሕያው ተስፋሁ ዕቀብኒ እግዝእትየ ለለመዋዕሉ ወርኁ እስመ ኢየአምር ሰብእ ዘይመጽእ ላዕሌሁ።

ማደሪያው አድርጎ የመረጠሽ አማናይቱ (እውነተኛይቱ) ታቦት አንቺ ነሽ። ከሥጋሽ ሥጋ ፤ ከነፍስሽ ነፍስ ነስቶ ኢየሱስ ክርስቶስ ካንቺ ተወልዷልና። እመቤቴ በየጊዜውና በየሰዓቱ ጠብቂኝ። ሰው በራሱ ላይ የሚመጣውን ነገር አያውቅምና።

መቅደስ አንቲ ዘይኬልሉኪ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕሉ ለእግዚአብሔር ቃል። ማርያም ድንግል መክሐ ደናግል ሰላም ሰላም በምልዓ ሕሊናየ እብል ለልደትኪ ፍሥሓ ወሣህል።

በእግዚአብሔር ቃል ሥዕል የተሣሉ ፤ ኪሩቤል የሚጋርዷት አማናይቱ (እውነተኛይቱ) መቅደስ አንቺ ነሽ። የደናግል መመኪያ ፣ ድንግል ማርያም ፣ ይቅርታና ደስታ ላለበት ልደትሽ በፍፁም ልቦናዬ ሰላም ሰላም እላለሁ።

አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ቀይሕ እንተ ውስቴታ መና ብሩህ። ማርያም ታቦት ዘተከለልኪ በንጽሕ አድኅንኒ እግዝእትየ እማየ ሙስና መፍርህ ከመ አድኃንኪዮ ቀዳሚ ለኖኅ።

በውስጧ ብሩህ መና ያለባት የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ። በንጽሕና ፣ በቅድስና ያጌጥሽ ድንግል ማርያም ድሮ ኖኅን ከጥፋት ውኃ እንዳዳንሽው እመቤቴ ማርያም እኔንም አድኝኝ።

አንቲ ውእቱ ተቅዋመ ወርቅ ዘትነብሪ ብርሃኖ ለዓለም ዘትፀውሪ። ኦ ድንግል መሐሪት እመ መሐሪ ኃጥአነ እለ ከማየ አመ ይኴንን ፈጣሪ ለአድኅኖትየ ማርያም ሥመሪ።

እውነተኛውን የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን የተሸከምሽ ፤ ለዘላለም የሆንሽ እውነተኛይቱ (አማናዊቱ) የወርቅ ተቋም ድንግል ማርያም ነሽ። ፈጣሪ እንደ እኔ የመሰሉት ኃጢአተኞችን በሚፈርድበት ጊዜ የምሕረት አምላክ እናት ፤ መሐሪ የሆንሽ ድንግል ማርያም እኔን ለማዳን ውደጂ።

አንቲ ውእቱ ማዕጠንተ ወርቅ እግዝእትየ ፍሕመ መለኮት ብቍጽ እንተ ዲቤኪ ተወድየ። ማርያም ድንግል ደመና ብዕልየ በዝናመ ሣህልኪ ሐረገ ወይን ፀገየ ወሮማንሂ ሐዋዘ ፈረየ።

ልዩ ንፁሕ የመለኮት ፍሕም የተጨመረብሽ ፣ የወርቅ ማዕጠንት እመቤቴ አንቺ ነሽ። ድንግል ማርያም የብዕሌ (ብልጽግናዬ ) ደመና አንቺ ነሽ። በንጽሕናሽ ዝናም ሐረገወይን አበበ። ሮማንም መልካም ፍሬን አፈራ።

የአዶናይ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ፤ የምሥራቃዊው ገነት እርግብ ማርያም ደስ ይበልሽ። ከእሴይ ሥር ፣ ከተመረጠው ዳዊት ግንድ የበቀልሽ መዓዛሽ ያማረ ፣ የወደደ ፣ ማርያም አበባ ፣ የማሕፀንሽ ፍሬ ወልድን ድሀው ሁሉ ተስፋ ያደርገዋል።

በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ዘእንበለ ተክል ቀዳሚ ምሳሌኪ ኮነ በሥምረተ አምላክ ቀዋሚ። ስእለተ ነዳያን ማርያም ዘኢትጸመሚ አስተበቍዓኪ በዕለተ ምንዳቤ ማሕመሚ ውስተ የማንየ ለነዳይ ትቁሚ።

ሳይተክሏት ተተክላ ፣ ውኃ ሳይጠጧት አብባ ለምልማ እንደተገኘችው የዓሮን በትር ፣ በሕያው አምላክ ፈቃድ ምሳሌሽ እንዲሁ ሆነ። የነዳያንን ልመና ችላ የማትዪ ድንግል ማርያም በአስጨናቂው የችግር ቀን በእኔው በድሀው ቀኝ ትቆሚ ዘንድ እማልድሻለሁ።

ለኪ ይደሉ ውዳሴ ወስባሔ በአፈ መላእክት ወሰብእ ዘይትረከብ ውስተ ኲለሄ። ማርያም ድንግል ማርያም እመ ኤሎሄ ከመ ለብሐዊ ፍቁርኪ አቅረብኩ እማኄ ለዝክረ ስምኪ ዘምዕዝ እምርኄ።

የኤሎሄ እናት ድንግል ማርያም ፣ በሁሉም ቦታ በሚገኙት መላእክትና የሰው ልጆች አንደበት ፍፁም ምሥጋና ይገባሻል። እንደወዳጅሽ ለብሐዊው (አንጥረኛው) ቅዱስ ኤፍሬም መዓዛው ከሽቶ ለሚበልጠው ለስምሽ አጠራር እጅ መንሻን አቀርባለሁ።

ስብሐት ለኪ ማርያም በኈልቈ አድባር ወአውግር። ስብሐት ለኪ ማርያም በኈልቈ ቀላያት ወባሕር። ስብሐት ለኪ ማርያም በኈልቈ ዕፀው ወሣዕር። ስብሐት ለኪ ንግሥተ ፍቅር በልሳነ ኲሉ ፍጡር። እስመ ምሉዕ ስብሐትኪ በሰማይ ወምድር።

ልጅሽ ውዳጅሽ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲምረን ፤ በቀኙ እንዲያቆመንና የርስቱ ወራሾች እንዲያደርገን ፤ የጌታችን እናትና እናታችን ድንግል ማርያም ስለእኛ ብለሽ ለምኝልን ፤ ለምኝልን ፤ ለምኝልን።

ማርያም በተራሮችና በኰረብታዎች ቁጥር ልክ ምሥጋና ይገባሻል። ማርያም በጥልቆችና በባሕሮች ቁጥር ምሥጋና ይገባሻል። ማርያም በዛፎችና ሣሮች ቁጥር ልክ ምሥጋና ይገባሻል። ንግሥቴ ሆይ በፍጡራን አንደበት ሁሉ ምሥጋና ይገባሻል። በሰማይና በምድር ምሥጋናሽ የመላ (ምሉዕ) ነውና።

ተፈሥሒ ማርያም ርግበ ገነት ጽባሐይ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ። አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ ዘሠረፅኪ እምሥርወ ዕሤይ ወእምጕንደ ዳዊት ኅሩይ ፍሬ ማኅፀንኪ ይሴፎ ነዳይ።