colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

አቤቱ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ! በቃለ ወንጌልህ «ለምኑ ይሰጣችኋል” ብለሃልና በቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት አምኜ ከሥጋና ከነፍስ ቁስል እድን ዘንድ ስፀልይ ይህን የልመናዬን ቃል አድምጥ። ጩኸቴንም አስተውል። ንጉሤና ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ሁል ጊዜ በማለዳ በፊትህ ቆሜ የምትሰጠኝን ለመቀበል እነሆ የወዳጅህ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የመልክእ ምስጋናን ማቅረብ እጀምራለሁ።

በስመ እግዚአብሔር

የአምልኮት ፍቅሩ ሐቅለ ሕሊና በሚያቃጥል በእሳታዊ እግዚአብሔር ስምና፤ ይህን ከንቱ ሰነፍ ዓለም በአማላጅነት ድንቅ ጥበቡ በምትፈውስ በኹለት ወገን ድንግል የምትኾን አምላክን በወለደች በድንግል ማርያም ስም ጽልመተ አበሳን የምታስወግድ የብርሃን መቅረዝ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ቸርነትህን እመሰክር ዘንድ አዋጅ ነጋሪ ቅዱስ አንደበትህ በአየረ ሰማይ በልዕልና ጎልቶ ይሰማ። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! አዋጅ ነጋሪ በኾነ በቅዱስ አንደበትህ የንስሓ ትምህርተ ስብከት ከሰዎች ላይ የኃጢአት ሸክምን እንዳስወገድክ ከእኔም ከአገልጋይህ ላይ የሚያሰቃየኝን ጽኑእ የኃጢአት ክምር አስወግድልኝ።

ሰላም ለፅንሰትክ

ያለኃጢአትና ያለርኩሰት በቅድስና ሕግ ለተፈጸመ ፅንሰትህ እና በወርኃሰኤ በሠላሳኛው ዕለት ለሚከበር ልደትህ ሰላምታ ይገባሃል። የሰማይ ደመናን ታዝዝ ዘንድ ሥልጣን የተሰጠህ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! በልቤ ውስጥ ተሰብስበው በአንድነት ወደ ከተማቹት ህዋሳቶቼ የጥበብ እንጀራንና ሰማያዊ መናን አዝንምልኝ። «በመወለድህ ሰው ኹሉ ደስ ይለዋል» ተብሎ ተነግሮሃልና ሉቃ. ፩. ፲፭ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔ ወጃጅህ በቅድስና የፀነሰችህ እናትህ ቅድስት ኤልሳቤጥን አባትህ ቅዱስ ዘካርያስንም በፍቅር አስባቸዋለሁ። መስከረም ሃያ ስድስት ዕለት ፅንሰትህ ሰኔ ሠላሳም ዕለት ልደትህ በመኾናቸው እኒህን ዕለታትም በደስታ እዘክራቸዋለሁ።

ሰላም ለዝክረ ስምከ

ደጋንና ሞገስን በተመላ በቅዱስ ገብርኤል አንደበት ለተመሰገነ ለስምህ አጠራር ሰላምታ ይገባል። ስለክፉ መሪር ኀኬቷ ይህቺን ከንቱ ዓለም የናቅህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እጅግ የበዛ የኔን በደልና የሥጋ ለባሽ ፍጡራንንም አበሳ ኹሉ ትደመስስ ዘንድ ቅድስት ጸሎትህ ወደ ሰማይ ትወጣ። ፀጋውንና ግርማ ሞገስን በተጎናፀፈ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የተፀነስህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ «የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና» እኔ ባሪያህ በኃጢአት ታስሬ እንዳልሞት አስበኝ።

ሰላም ለስእርተ - ርእስከ

ምስጋና ለሚገባው ለራሱ ፀጉርህና እንደ ሞፈር እንጨት ለተቆረጠ ራስህ ሰላምታ ይገባል። የመጥቅዕና የአበቅቴ መጀመሪያ ርእስ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ቅዱሳን መላእክትና ኃዘንተኛ መዋቲ ሰውን የሚያስደስት ጥዑም የድድቅህ ዜና መብል ከጥዑም የጽድቅህ ዜና መብል ከጥዑም የጽድቅህ መጠጥ ጋራ እኔን ሕሙም በሽተኛአገልጋይህን ይፈውሰኝ። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ መስከረም አንድ ቀን የዓመታት የአዉራኀና የዕለታት መጀመሪያ ትኾን ዘንድ የተሾምክበት ዕለት በመኾኑ ይህን የዓውደ ዓመት ዕለት ሳስብ እደሰታልሁ። ቅዱስ አንገትህ በርጉም ሔሮድስ ተቆርጦ ያፈረበትን መስከረም ሁለት ቀን ሳስብ ደግሞ አለቅሳለሁ። ነገር ግን ሞትህ ክብርህ ስለኾነ የምጽናና እኔ አገልጋይህ በሰላም በጤና ከዓመት ወደ ዓመት እሸጋገር ዘንድ በጸሎትህ እርዳኝ።

ሰላም ለገጽክ

እንደ አምላክ እንደ ኤሎሄ ለሚያደለድል ብሩህ ፀዳል ፊትህ ሰማያዊ ብርሃንም ለከበባቸው ቅንድቦችህ ሰላምታ ይገባል። በምሥራቅ ገነት የተተከለች የምሥራቅ ተክል መዓዛ የሆንህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ፀዳሉ እስ እስኪደነቅ ድረስ ውበቱ ዘለዓለማዊ የኾነ የኾነ የፊትህ ሞገሳዊ ቅላት በፊቴ ላይ ይበዛ ዘንድ እለምንሃለሁ። የገነት ተክል ሽቱ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔ ባሪያህ የዚህ ከንቱ ዓለም መዓዛ አላስደሰተኝምና አንተ በምትኖርበትና የጽድቅ መዓዛ ሽቱ ባለበት ገነት ውስጥ እንድኖር ለምንልኝ።

ሰላም ለአዕይንቲ

ብሩሃት ለኾኑ ኹለት ዓይኖችህና በአንድነት ላሉ ኹለት ጆሮዎችህ ሰላምታ ይገባል። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ትጉህ መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤልና ጻድቅ ኢዮብ መለኮትን ሊያጠምቁ ቢወዱና ቢተጉም የባሕርይ አምላክ ነዳዲ እሳት ኢየሱስ ክርስቶስን ያጠምቁ ዘንድ አልተቻላቸውም። የብርሃናት አለቃ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ራፋኤል በትጋቱና ጻድቅ ኢዮብም በጽድቁ እንዲያማልዱኝ እማፀናቸዋለሁ። ዳግመኛ ከእነሱ ይልእሳተመለኮተ ጌታን ለማጥመቅ የታደልክ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔን አገልጋይህን በማየ ንስሓ ታጥበኝ ዘንድ እለምንሃለው።

ሰላም ለመላትሔክ

በምድረ በዳ የንስሓ ትምህርት ስብከትን እያስተማርህ ሳለህ በፀሐይ ሐሩር ለጠወለጉ ጉንጮችህ መንታ ለኾኑ አፍንጫዎችህም ሰላምታ ይገባል “ዕልዋ” የተባለ የሽቱ ዓትነት ስም ያለህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እንደ ብዙ ምርኮ ደስ የሚያሰኝ ቃል ኪዳንህ የመላእክትን ልብና የሰውን ሕሊና በኃሤት ይመላል። በዮርዳኖስ በረሀ ስለሃይማኖት የተረከራተትህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔም በቅድስት ተዋሐዶ ሃይማኖት እፀና ዘንድ እርዳኝ።

ሰላም ለከናፍሪከ

የፍጡራን ከንቱ ሃሳብ ለለወጡ ከናፍሮችህና የበፀል ምግብን ላልቅመሱ አፍህ ሰላምታ ይገባል። ወርቅም የምታስንቅ ዕንቁ ባሕርይ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! በኹለት ወገን /በሥጋም በሀሣብም/ ድንግል የምትኾን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ፀንሳ ሳለ በጎበኘቻችሁ ጊዜ በእናትህ ማኀፀን ኹነህ ለልጇ ለባሕርይ አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስና ለክብርት እናቱ ለወላዲተ አምላክ ሰገድህ። እክለ አበሳን ያልቀመስህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ድንግል ማርያም ጌታን በማኀፀኗ ተሸክማ ከእናትህ ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር እጅ ሲነሳሱ ለአምላክህ በደስታ እየዘለልክ እንደሰገድህ እኔም ባሪያህ ለፈጣሪዬ አዘውትሬ እሰግድ ዘንድ እንድተጋ እርዳኝ።

ሰላም ለአስናኒክ

ሳቅ ሥላቅን ላለመዱ ጥርሶችህንና የመዘበት ከንቱ የዋዛ ቃልን ላልተናገር አንደበትህ ሰላምታ ይገባል። ኃላፊ ወርቅን የናቅህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የክቡር በዓልህ የምስጋና እምቢልታ በተነፋ ጊዜ ነጎድጓድን ያመጣል። መብረቅንም ያስከትላል። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በየወሩ በሁለተኛው ወይንም በሠላሳኛው የበዓልህ ዕለት ብቻ ሳይኾን ዘወትር “ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ ዮሐንስ” እንድልህ በእኔ በአገልጋይህ ላይ ፍቅርህን አሳድርብኝ።

ሰላም ለቃልከ

አነጋገሩ ላማረና ለተወደደ ቃልህ እሳተ ላህቡም ለሕሙማን ፈውስን በመስጠት ለሚያስደስት እስትንፋስህ ሰላምታ ይገባል። የእግዚአብሔር ባለሟል ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የቃል ኪዳንህ ወርቅ ለድኃ መዝገቡ ለሰነፍም ጥበቡ ነው። በፈውስ ጥበብህ ለሕሙማን ደስታን የምታጎናጽፍ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔ ባሪያህ በሐብለ ኃጢአት ታስሬ እንዳልሞት በቃል ኪዳን በከበረው እስትንፋስህ ያደረብኝን ጽኑእ ሕመም እፍብለህ ሰውነቴን ትፈውስ ዘንድ እማጸናለሁ።

ሰላም ሰጉረዔከ

ጥዑም ቃል ለሚፈስበት ጉሮሮህ ዳግመኛም በምስጋና ማእተብ ለተሸለመ አንገትህ ሰላምታ ይገባል። የወይነ ጋዲ ፍሬ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የዓመፃ ንጉሥ ጠላት ሄድሮስ አንገትህን ባስቆረጠ ጊዜ ወላጅ አባትህ ቅዱስ ዘካርያስ ምኝና አዝኖ ኑሯል? በአየር ላይ እየተዘዋወርህ ለማስተማር ትችል ዘንድ እንደ መላእክት ክንፍ የተሰጠህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የዚህ ዓለም ኑሮ ከንቱ እንደኾነ አምኜ እንድከተልህ ለእኔ ለወዳጅህ ወደ ፈጣሪዬ የምበርበት ክንፈ ጸጋህን በልቤ ውስጥ ፍጠርልኝ።

ሰላም ለመታክፍተክ

የዚህ ዓለም ኃላፊ የደስታ ቀንበር ለጣሉ ትከሻዎችህና የግመል ፀጉርን ልብሱ ላደረገች ጀርባህ ሰላምታ ይገባል የተስፋና የበረከት መዝገብ ድንግል ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ከባሕርይ አባቱ ከአብ፤ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረና የሚኖር ኢየሱስ ክርስቶስ የአንተን ክብር በነገራችወ ጊዜ ቅዱስ ያዕቆብ ተደሰተ። ኬፋ የተባለ ቅዱስ ጴጥሮስም በኃሴት ተመላ። የመንግሥት ሰማያት መዝገብ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔ ከቤተሰቦቼ ጋር ከቅድስና ሕይወትህ ተምረን በመንግሥተ ሰማያት ዘንድ መንፈሳዊ ሕይወትህን እያሰብኩ እለምንሃለሁ።

ሰላም ለእንግድእከ

የፀጋ አዝመራ ነዶዎቹን ላቀፉ ደረትህ እና እንደ ትከሻህ ለሚያምር ሕጽንህ /እቅፍህ/ ሰላምታ ይገባል። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ከአምላክ ተሰጥቶህ ቅዱስ ያዕቆብ ከጻፈውና አምላክ ከሰጠህ ቃል ኪዳንህ አንዱ ከሚጎድል ሰማይና መድር ቢያልፉ ይቀላል። የፀጋና የበረከትን ነዶ የምትሰጥ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ከእኔ ከአገልጋይህ የጌታዬና የአምላኬ የኢየሱስ ክርስቶስ የመዳን ጸጋው እንዳይለየኝ በፀሎትህ በአማላጅነትህን እርዳኝ።

ስላም ለአእዳዊከ

የኃጢአት አዘቅትን ላልቆፈሩ እጆችህና በአምላክ ራስ ላይ ለረበበ /ላረፈ/ ክንድህ ሰላምታ ይገባል። ይገዛልህ ዘንድ አውሬ ሰይጣንን በሥልጣነ ጸጋ የምታስር ሞገስን የተመላህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ አቤቱ የጥበበኛ ሰው ምሳሌ እኾን ዘንድ ንጹሕ ሕሊናን፤ ቅን ልቡናን በጸሎትህ አድለኝ። በተሰጠህ ሥልጣን አራዊትን የምታስር ቅዱሱ ዮሐንስ ሆይ በዚህ ዘመን የሰው ልጀ ኃኬት ከአራዊት ባሕርይ ብሷልና የሰው ልጆች ኹሉ ከኃኬት ከክፋትና ከተንኮል ይርቁ ዘንድ መልካም ልቡና እንድትሰጣቸው እኔ አገልጋይህ እለምንሃለሁ።

ሰላም ለኵርናዕከ

እንደ ሌላው ቅዱስ አካልህ ለተዋቡ ክብራት ክንዶችህ፤ በአንድነትም ለበቀሉ ክርኖችህ ሰላምታ ይገባል። የሚያስደንቅ የአምላክህን ድምፅ አዘውትረህ የምትሰማ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የደስታ መልእክተኦች ክበርህና ቸርነትህ በየመልኩና በየክርሉ ካንተ ዘንድ ታዘው ወደኔ ይምጡልኝ። «የእግዚአብሔርን ጎዳና ጥረጉ አዘጋጁ።» ብለህ በምድረበዳ ያስተማርህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! እኔ ባሪያህ በዮርዳኖስ በሚፈልቅ ማየአእምሮ ሰውነቴን ታጥብ ዘንድ እለምንሃለሁ።

ሰላም ለእራኃከ

በሠራዊተ ሰማይ የሚመሰገን እግዚአብሔር ላመስግነው ቅዱስ መሐል እጅህና በዮርዳኖስ ውኃ ያጠምቁት ዘንድ እሳተ መለኮት መድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ለዳሰሱ እጆችህ ሰላምታ ይገባል። ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ከሕሊናው በፈሰሰ ደስ የሚያሰኝ የዕውቀት ውኃ ይቀድሰኝና በመንፈሱም ያነጻኝ ዘንድ ወደ መምህርህ ወደ ኢያሱ ጸልይልኝ። መለኮትን የዳሰሰኽ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ሰዎችን ለመርዳት የተፈጠርኽ ነኽና የእኔ የወዳጅህን ሕማም በፈውሰ ረድኤትህ እንድትዳስስልኝ እለምንሃለሁ።

በሰላም ለአጽፋሪ እዴከ

እንደ ዳርቻማ ሥፍራ በእጅህ ጫፍ በሚገኙ ጥፍሮችህንና የደስታ ምንጣፍን ለማይሻ ጎንህ ሰላምታ ይገባል። የክርስቲያን እምነት መርከን የምትቀዝፍ ጠቢበ ሃይማኖት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ከኃላፊው የሰው ልጅ ትውልድ ውስጥ ይቅርና ፈጣሪህ እንደተናገረው ሱፊፊ የተባለው መልአክ ስንኳ በሰማይ በክብር አይስተካከልህም። ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃልን በሰዎች ልቡና የምትዘራ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በእኔና በቤተሴብኤ ላይ የሃይማኖት ፋናን እያበራህ ለመንግሥተ ሰማያት ታበቃን ዘንድ

ሰላም ለከርሥከ

ሥርዓትንና ሕግን ለመረጠ ሆድህና ከበቀላን ከክፋት ለራቀ ልብህ ሰላምታ ይገባል፡፤ እንደ ኖኀ ተረፈ አበው ተብለህ የምትጠራ ንጹሕ የአረጋውያን አበው ምትክ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ብዙ የሥቃይና የመከራ ወንዞች በአንድነት መልተው ቢፈሱ እንኳ ከእኔ ከወዳጅህ ዘንድ የፍቅርህን እሳት ፈጽሞ ሊያጠፉትአይቻላቸውም። ከቂም በቀልና ከኃጢአት የነጻህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ጠላትህንም አፍቅር በተባለ ሕገ እግዚአብሔር መሠረት እግዚአብሔር ፍቅር መኾኑን የምረዳው ይህንን ፈጽሜ ስገኝ ነውና እኔ ፍጡራን የኾኑ የሰው ልጆችን ኹሉ እንድወድ በፍቅር ጎዳና ምራኝ።

ሰላም ለኵልያቲከ

ከአምላክ ልቡና ጋር ለሚስማማ ኵላሊትህና ሳይቅበዘበዝ በፀጥታ ለሚኖር ሕሊናህ ሰላምታ ይገባል። ዓለምን የናቅህ ንጹሐ ግብር ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በተጋድሎ የሥቃይ ግብረ ሕማም አንተን የሚመስለው ዬማዕታት ሹም ተርቢኖስ የተባለው የመንፈስ ወንድምህ ሊቀ ሰማዕታት ነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋራ እኔን በቅድስት ተዋሕዶ እምነቴ እንድጸና በአማላጅነታችሁ ትረዱኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

ሰላም ለአማዑቲከ

የሥጋህ መሸፈኛ ለጋረደው ንዋየ ውስጥህና እግዚአብሔር በእጁ ለሠራው አንጀትህ ሰላምታ ይገባል። ጥበብና አእምሮህን የተመላ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ፍጹም የተዋቡ የደንጊያ ሕንፃ ቤቶችን ንቀህ በዱር በገዳም የመኖር ጋዓር እንደምን አላደከመህም? ጥበብና አእምሮን የተመላ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የጥበብ መጀምሪያ እግዚአብሔርን በመፍራት እኖር ዘንድ በአማላጅነትህ እርዳኝ።

ሰላም ለኀንብርትከ

የዘለዓለም አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስን ግብረ ጥበብን የሚያስመሰግን እንብርትህና የማስተዋል ትጥቅን ለታጠቀ ወገብህ ሰላምታ ይገባል። በሃይማኖት ለእነ ቅዱስ ቂርቆስ ወገናቸው የኾንኽ የእግዚአብሔር ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! በተሰጠህ እውነተኛ ቃል ኪዳንህ ታምኖ ንስሐ የገባ ሽፍታ ስንኳ ዳግም ሞት ፈጽሞ ይድናል። የሃይማኖት ዝናርን የታጠቅህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ በባሕርየ ገድላቸው አንተም የሚመስሉ እነ ቅዱስ ቂርቆስ ስለሃይማኖት ብለው ባለፉት የመከራ ፍኖተ ገድል ሳልፈራ ጸንቼ እንድጓዝ እኔ ልጅህን የሃይማኖት ዝናርህን አስታጥቀኝ።

ሰላም ለአቁያጺከ

በተወደደ የምስጋና ቃሉ ማኀሌት ለከበሩ ጭኖችህ ዳግመኛም ለጽኑኣት ጉልበቶችህ ሰልማታ ይገባል። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! የአምላክህ የኢየሱስ ክርስቶስን ምስጋና ከጧት እስከ ማታ ሳታቋርጥ የምታመሰግነው አንተ ፈጣሪውን አዘውትሮ የሚያሰመሰግን ሊቀመላእክት ቅዱስ ራጉኤልን ትመስላለህ። ዝንጋኤ በሌለው ልቡና ፈጣሪን ለማመስገን የተመረጥህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ፈጣሪን ለማመስገን እችል ዘንድ አዲስ ልቡናን በአማላጅነትህ ትፈጥርልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።

ሰላም ለአእጋሪክ

በበረኃ ውስጥ በብቸኝነት ለኖሩ እነግሮችህና ያለድካም ሳያቋርጡ በመመላለስ ለፀኑ ተረከዞችህ ሰላምታ ይገባል። የበደልን ትቢያ የምትበትን ኃይል ዓውሎ ነፋስ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ያንተን ነገር ማሰብ ሕሊናዬን ማረከው። የፍቅርህ እሳትም ልቤን እንደ ሰም አቀለጠው። በተሰጠህ የፀጋ አምላክነት ሥልጣን የኃጢአትን በደል እንድታጠፋልኝ፤ የአንተን ፍቅር በውስጤ ሳወጣ ሳወርድ፤ በፍቅርህ ጸንቼ እንድኖር ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ኃጢአትን ከእኔ ከወዳጅህ ላይ ለማስወገድ በፍቅር ጎዳና ወደ ፈጣሪ ምራኝ።

ሰላም ለመከየድክ

ዘወትር በትጋት ለሚቆም ለጽኑ የእግርህ መርገጫና የአእዋመ ሥጋ ጫፎች ለኾኑ ጣቶችህ ሰላምታ ይገባል። የባሕርይ አምላክ የኢየሱስ መልእክተኛ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ለአንተ በተሰጠ የእውነት ቃል ኪዳንህ ምክንያት ብዙዎች ያለብርና ወርቅ በእፍኝ ውኃና እሁለት ትንሽ የሣንቲም መጽዋት መንግስተ ሰማይን ይወርሷታል። ከተሰጠህ ቃል ኪዳን የተነሳ በእፍኝ የውኃ ምጽዋት መንግሥተ ሰማያትን የምታሰጥቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔ ወጃጅህ የጌታን ቃል በመፈጸም የመንግሥተ ሰማይ ወራሽ እንድኾን አብቃኝ።

ሰላም ለአጽፋረ እርግከ

ጽዱላት ለኾኑ ለእግርህ ጥፍሮችና ለተዋበ ጽኑእ ቁመትህ /አቋቋምህ/ እልል እያልኩ የምስጋናዬን ሰላምታ አቅርብልሃለሁ። ለስምህ ጸጋና ሞገስ የተሰጠው የክርስቶስን መርካ መስቀል የተሸከምህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ፆፈ ነድ እንደሚሰኝ የእሳት ክንፎች እንዳሉት እንደ ቅዱስ ራጉኤል አምላክህን ለማመስገን በዙፋኑ በስተቀኝ በመንበሩ አጠገብ የምትቆም አንተነህ። በክርስቶስ ደም የከበረ መከራ መስቀሉን የተሸከምህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ እኔ ወዳጅህ በዚህ ዓለም ሳለሁ በሃይማኖቴ እጸና ዘንድ እርዳታህን እንዳይለየኝ። ሊቀመላእክት ቅዱስ ኡራዔልም ከእኔ ሳይለይ በክንፈ ረድኤቱ እንዲጠብቀኝ እለምናለሁ።

ሰላም ለመልአክ

በጣፋጭ ምስጋናና በጥዑም ዝማሬ ለከበረ መልክህና በብሩህ የሰማይ ደመና ድንኳን ውስጥ ለተጋረደ የቅድስት ነፍስህ እርገት ሰላምታ ይገባል። ወራውሬ ከተባለ ፀአዳ ዕንቁ ይልቅ የከበርህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ምድር አፏን ከፍታ የዋጠቻቸው እኩያን የቆሬ ልጆች ወዳሉበት ጠላቶቼን አውርዳቸው። በንጽሕና ከወርቅና ከዕንቍ ይልቅ የጠራህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ፍፁም የጠራህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ፍፁም በኾነ እምነት ፈጣሪህን የተማፀነ፤ አንተንም በአማላጅነት አምኖ የለመነ ጠላቶቹ ኹሉ እንደ ጢስ ተነው ይጠፋሉና የእኔም የወዳጅህ ጠላቶች ከእኔና ከቤተሰብኤ ይርቁ ዘንድ የማስተዋል ፍቅርንና መልክማ የሰላም ልቦናንም እንዲያገኙ እማፀናለሁ።

ሰላም ለበድነ ሥጋሁ

በንጹህ ግንዘተ ሥጋ ለተገነዘ ለቅዱስ በድነ ሥጋህ ዳግመኛም የሰማይ የብርሃን ክዋክብት ጌጥን ለተሸከመ መቃብርህ ሰላምታ ይገባል። ጣፋጭ ፍሬን ያፈራህ የገነት ተክል መልካም ዛፍ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ይህን ያንተን የመልክህን ስም የሚንቅና የሚያቃልል ፍጡር በሰውና በመላእክት አፍ ተለይቶ የተወገዘ ይሁን። የቅድስና ፍሬ መዓዛን ያፈራህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የንጽሕናን ሰላማዊ ፍሬ እመገብ ዘንድ ደስ እንዲያሰኝ የምለምንውም ኹሉ እንዲፈፀምልኝ የሥራዬም ትርፍ እጥፍ ይሆንልኝ ዘንድ ቅዱሳን መላእክትም አብረውኝ እንዲቆሙ እኔ ያንተ ወዳጅ የአማላጅነትህን ፀጋ እማፀንሃለሁ።

አምኃ ስብሐት

በአራት ሱባዔ ልክ የእያንዳንዱን የመልክህን ስም እየጠራሁ በመቍጠር እነሆ ልዩ የምስጋና እጅ መንሻን ሃያ ስምንት ጊዜ ለመልክአ አካልህ ኹሉ አቀረብኩልህ። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ የወንጌል ጉባዔ መለከት ከሚኾን ከወዳጅህ ከቅዱስ በርተሎሜዎስ ጋር ኾነን የኹላችን ጌታ የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌላዊት አውደ ምሕረት ጸሪቀ መበለትን እንደተቀበለ ኹሉ የእኔንም ይህን ያቀረብኩልህን ልመና ተቀበለኝ። በተሰጠህ ቃል ኪዳን፤ በክብሩ የአማላጅነት ልመናህ በቅዱስ ማየ ፀበልህ የገላዬን ቁስል የምትጠግን፣ የሕሊናዬን ሕመምና የምትፈውስ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! የነፍሴንም ቁስል በቃል ኪዳንህ ፈውሰህ እኔ ባሪያህን­­­ ለመንግሥተ ሰማያት አብቃኝ አሜን። ልቤን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ!! ስለ እኛ ወደ አንተ በሚቀርበው የቅዱስ ዮሐንስ የአማላጅነት ለመና አንድን ዘንድ የአገልጋይህ የቅዱስ ዮሐንስን ስም በምስጋና እንድንጠራ ፈቅደህ ርቱዕ አንደበትን ስለሰጠኸን አቤቱ እናመሰግንሃለን፡፡ አቤቱ እናከብርሃለን። አቤቱእንገዛልሃለን። አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመሰግናለን። ጉልበት ኹሉ የሚሰግድልህ አቤቱ እንሰግድልሃለን፡፡ አንደበትም ኹሉ ለአንተ ይገዛል። የአማልክት አምላክ የጌቶችጌታ፣ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ። የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ አንተ ነህ። እናንተ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ብላችኹ ፀልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።