ዋዜማእግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ ወተወልደ ቃለ ጽድቁ ለአብ፤ ማርያምሰ ተሐቱ፤ ውስተ ከርሡ ለአዳም፤ ከመ ባሕርይ ፀዓዳ ፤ ፆረቶ ፤ እግዝእቱ ለአዳም ማርያምሰ ተሐቱ፤ውስተ ከርሡ ለአዳም፤ ከመ ባሕርይ ፀዓዳ ፤ ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም፡፡ በሐምስሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኀረያ ሰአሊ ለነ ማርያም |
እግዚአብሔር ነግሠደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፤ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፤ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፤ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፤ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ በሐምስዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን፡፡ |
ይትባረክእግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡ ሰላምሃሌ ሉያ (3) ፃኢ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት ርቱዕ አፍቅሮትኪ፤ ቡርክት አንቲ እምአንስት ማኅደረ መለኮት ፃኢ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፤ ወልድኪ ይጼውዓኪ፤ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡ (ዮሐ 17 ፥ 24) |
ማኅሌትሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡ ዚቅወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፤ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኵኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም ፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ |
ነግሥእምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤ ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን፤ አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤ ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን ፤ እመቅድሀ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን ፤ ወበውስቴታ ተሠርዓ ቊርባን፡፡ ዚቅዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል፤ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን ፤ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጐላት ፤ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፤ እንተ ሠረፀት ለሕይወት፡፡ |
መልክአ ኪዳነ ምሕረትሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ተሐደሰ፤ እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤ ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቊዓኪ አንሰ፤ ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤ እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡ ዚቅደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፤ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፤ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፤ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፤ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ |
መልክአ ማርያምሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤ እምነ ከልበኒ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትእዛዝ፤ ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ ከመ ይሰቅዮ ውሒዝ ለሠናይ አርዝ፡፡ ዚቅሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፤ ወልድኪ ይጼውዓኪ፤ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡ |
ሰላም እስትንፋስኪ ዘመዐዛሁ ሕይወት ከመ መዐዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት፡፡ ዚቅንዒ ኀቤየ እንቲአየ፤ ሠናይት ርግብየ፤ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡ |
መልክአ ፍልሰታሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ ወዘኢይነጽፍ ባሕርየ ተውዳሱ ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ ፡፡ ዚቅማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤ ማኅደረ መለኮት እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ሰማያዊት እንተ በምድር ታንሶሱ፡፡ |
ምልጣንትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤ ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፤ ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፡፡ እስመ ለዓለምበአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ እምወይን መዓዛ ዕፍረትኪ እምኵሉ አፈው እትፌሳሕ ወእትሐሠይ ብኪ ናፍቅር አጥባትኪ እምወይን ርቱዕ አፍቅሮትኪ ኵለንታኪ ሠናይት እንተ እምኀቤየ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት ፡፡ |
ቅንዋት (ቅዳሜ የሚባል)ክብሮሙ ለቅዱሳን ሞገሶሙ ለጻድቃን መርሖሙ ለዕውራን ዝንቱ ውእቱ መስቀል እንስሳ ገዳምኒ አዕዋፈ ሰማይኒ ያንቀዐድዉ ኀቤከ አምላክ መስተመይጥ፤ ያፀግብ ነፍሰ ነዳያን ያከርም በበዓመት፤ ለዘበእንቲአነ ውስተ ማኅፀና ለማርያም ተሠወርከ ወበደመናትኒ ሰማየ ዘከለልከ ወኵሊ ቀሊል በኀቤከ |