colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

የዘወትር ፀሎት

በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ መስቀል ፊቴን እና መላ ሰውነቴን ሦስት ጊዜ አማትባለሁ። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን(፫ ጊዜ ማማተብ) ፩፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማፀንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለሁ። በእዚች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቆሜ እክድሃለሁ። ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።

፪፤ አቤቱ እናመሰግንሃለን ፤ አቤቱ እናከብርሃለን ፤ አቤቱ እንገዛልሃለን ፤ አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመስግናለን ፤ ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ ፤ አቤቱ እንሰግድልሃለን ፤ አንደበትም ሁሉ ላንተ ይገዛል ፤ የአምላኮች አምላክ ፤ የጌቶች ጌታ ፥ የንጉሦችም ንጉሥ አንተ ነህ። የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ አንተ ነህ። እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።

አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግስትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን።የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል። አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግስት የአንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ፤ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሃሳብሽ ድንግል ነሽ፣ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአሸናፊው የእግዚአብሔር እናት ሆይ፤ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን መድኃኒትችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን እና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

የሃይማኖተ ጸሎት ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚስተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለርሱ ምንም ምን የሆነ የለም ስለኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ ፣ ደግሞ ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ፣ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፣ በቅዱሳት መጻህፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደሰማይ ዐረገ። በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፣ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም። በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱ ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ እና ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን ፣ እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረው ነው ከሁሉም በላይ ብምትሆን ሐዋርያት በሰበሰቧት (በሠሯት) በአንዲት ክብርት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።

አሸናፊ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ። ምስጋናህም በሰማይ በምድር የመላ ነው። ክርስቶስ ላንተ እንሰግድልሃለን ከሰማያዊ ከቸር አባትህ ጋራ አዳኝ ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ እንሰግድልሃለን ወደዚህ ዓለም መጥተህ አድነኸናልና።

ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ (3 ጊዜ በል) ። አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለሁ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለሁ፣ ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እስገዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው ፣ ኃይላችን መስቀል ነው ፣ የሚያፀናን መስቀል ነው ፣ መስቀል ቤዛችን ነው ፣ አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም።

ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል /3 ጊዜ በል/። አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል። ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል። ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ ዳግመኛም ፣ በመጣ ጊዜ እንዳያዳፍረን ፣ ስሙን ለማመስገን ያነቃን ዘንድ ፣ እርሱንም በማምለክ ያጸናን ዘንድ፣ እመቤታችን ጸሎታችንን አሳርጊልን ፣ ኃጢአታችንንም አስተሥርዩልን በጌታችን መንበር ፊት ጸሎታችንን አሳርጊልን ፣ ይህንን ኅብስት ላበላን ይህንንም ጽዋ ላጠጣን ምግባችንን እና ልብሳችንን ላዘጋጀልን ኃጢአታችንንም ሁሉ ለታገሠልን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለሰጠን እስከዚችም ሰዓት ላደረሰን ለእሱ ለልዑል እግዚአብሔር ፍፁም ምስጋና ይገባዋል ለወለደችውም ለድንግልም ምስጋና ይገባል። ለኢየሱስ ክርስቶስም መስቀልም ምስጋና ይገባል። የእግዚአብሔር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱ እና በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።

እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።

አምላክን በድንግልና የወለደች የእመቤታችን የማርያም ጸሎት ምርያምም አለች ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል። የባሪያይቱን መዋረድ አይቷልና። እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል። እርሱ ብርቱ የሚሆን ታላቅ ሥራን ለእኔ አድርጓልና ስሙም ቅዱስ ነው። ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ነው ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው አሳብ የሚኮሩ ትዕቢተኞችን በታተናቸው ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው የተራቡትንም በቸርነቱ አጠገባቸው ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው ምሕረቱን እንዲያስብ እስራኤል ባሪያውን ተቀበለ። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩም እስከዘለዓለሙ ድረስ እንደተናገረው።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ በሰንበተ ክርስቲያን እሑድ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

ከሴቶች ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ ፥ የተወደድሽ ተባልሽ፣ ከተለዮ የተለየች በዉስጧም የኪዳን የሕግ ጽላት ያለባት የምትባይ ሁለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ፣ ኪዳንም በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ዓሥሩ ቃላት ናቸዉ። ያለመለወጥ ካንቺ ሰዉ የሆነ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን መጀመሪያ ስሙን አስቀድሞ በየዉጣ ነገረን ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንጹሓን የሆኑትን ወገኖቹን አነፃቸዉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሁል ጊዜ ንጽሕት የሆንሽ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ፥ ሁላችን ስለዚህ እናገንሻለን ሰዉን በሚወድ በጌታ ዘንድ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እንለምንሻለን ወዳንቺም እናንጋጥጣለን። ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረፀ በዉስጥና በዉጭ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ያለመለየትና ያለመለወጥ ሰዉ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይመስልልናል። ይኸዉም መለወጥ የሌለበት ንጹሕ መለኮት ነዉ። ከአብ ጋር የተካከለ ነዉ ለንጽሕት በራሱ አበሠራት። በልዩ ጥበቡ ያለ ወንድ ዘር እንደ እኛ ሆነ መለኮቱን አዋሕዶ ያለ ርኵሰት ባንቺ ሰዉ ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

በእግዚአብሔር ሥዕል የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ። ንጽሕት ሆይ፥ ያለ መለወጥ ካንቺ ሰዉ የሆነዉ ቃል ኃጢአታችንን የሚታስተሠርይልንና አበሳችንን የሚደመስስልን ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የተሠወረ መና ያለብሽ የንጹሕ ወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ። መናም ከሰማይ የወረደውና ለዓለም ሁሉ ሕይወትን የሚያድለዉ ኅብስት ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሁል ጊዜ ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ። ይኸውም ፋና የዓለም ብርሃን ነዉ። ጥንት ከሌለው ብርሃንም የተገኘ ብርሃን ነው። ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው ያለ መለወጥም ከአንቺ ሰው የሆነው ነው። በመምጣቱም (ሰው በመሆኑም) በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለምንኖር እኛ አበራልን፣ በልዮ የጥበቡ ምሥጢር በሥጋዌ የልቦናችንን እግር ወደ ሰላም መንገድ አቀናልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።

ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለዉን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ። ፍሕም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው። ይኸውም ከአንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የእግዚአብሔርን ቃል የወለድሽልን መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፣ ከዕሴይ ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች። ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን እውነተኛ አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደ እርሷ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ጸጋን የተመላሽ ሆይ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል። አንቺ ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ። ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኚልን ነሽ። ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን፣ እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ሰኞ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነፃ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን ።

ከድንግል ያለ ወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና አዳነን። ከይሲ ዲያቢሎስ ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ፃርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት። ሰዉን ወደደና ነፃ አደረጋት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሰዉ የሆነና በኛ ያደረ ቃል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ። ክብሩንም ለአባቱ አንድ እንደመሆኑ ክብር አየነ። ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ነቢዩ ኢሳይያስ በመንፈስ ቅዱስ የአማኑኤልን ምስጢር አየ። ስለዚህም ሕፃን ተወለደልን፣ ወልድም ተሰጠልን ብሎ አሰምቶ ተናገረ ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሰዉ ሆይ ፈጽመህ ደስ ይበልህ፣ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና፣ አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና። ልዑል ክንዱን ሰደደልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የነበረዉ የሚኖረዉ፣ የመጣዉ ዳግመኛ የሚመጣዉም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ያለመለወጥ ፍጹም ሰዉ ሆነ። አንዱ ወልድ በሥራዉ ሁሉ አልተለየም፣ የእግዚአብሔር ቃል መለኮት አንድ ነዉ እንጂ፣ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የነቢያት ሀገራቸዉ ቤተ ልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ። ሁለተኛዉ አዳም ክርስቶስ በአንቺ ዘንድ ተወልዷልና፣ የቀድሞዉን ሰዉ አዳምን ከምድር (ከሲኦል) ወደ ገነት ይመልሰዉ ዘንድ። አዳም ሆይ መሬት ነበርህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት ፍርድ ያጠፋለት ዘንድ። ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሰዉ ሁሉ ሰዉነት ደስ ይላታል። በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰዉም እርሱ በሚፈቅደዉ እያሉ አሰምተዉ ንጉሥ ክርስቶስን ከመላእክት ጋራ ያመሰግኑታል፣ የቀድሞዉን እርግማን አጥፍቷልና። የጠላትን ምክሩን አፈረሰበት። ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸዉን ቀደደላቸዉ፥ በዳዊት ሀገር የተወለደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸዉ፣ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እዉነተኛ ብርሃን ስለ ሰዉ ፍቅር ወደ ዓለም የመጣህ። ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለዉ፥ አዳምን ከስሕተት አድነኸዋልና ሔዋንንም ከሞት ፃዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና። የምንወለድበትን መንፈስ (ረቂቁን ልደት) ሰጠኸን፥ ከመላእክት ጋርም አመሰገንህ ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ማከሰኞ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

1፥ የመመኪያችን ዘዉድ የደኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት እኛን ስለማዳን ሰዉ የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን። ሰው ከሆነ በኋላም ፍጹም አምላክ ነው፥ ስለዚህም በድንግልና ወለደችው። ድንቅ የሆነ የመውለዷ ችሎታ የማይመረመር (ሊነገር የማይችል) ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2፥ በእርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መጥቶ አዳነን። በድንግልና ፍጽምት የሆንሽ ማርያም ሆይ፥ የድንግልናሽ ምስጋናና ክብር ታላቅ ነው፥ እግዚአብሔር ካንች ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና። ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡባትና ሲወርዱባት ያያት መሰላል አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

3፥ ሙሴ በነደ እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ፥ ይኸዉም መጥቶ በማሕፀንሽ ያደረዉ የእግዚአብሔር ልጅ ነዉ። የመለኮቱ እሳትነት ሥጋሽን አላቃጠለውም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

4፥ ዘር ያልተዘራባት እርሻ አንቺ ነሽ፥ የሕይወት ፍሬ ከአንቺ ወጣ። ዮሴፍ የዋጃትና የከበረ ዕንቁን ያገኘባት ሣጥን አንች ነሽ፥ ይኸዉም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በማሕፀንሽ አደረ፥ በዚህ ዓለምም ወለድሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

5፥ የመላእክት ደስታቸዉ የሆነ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። የነቢያት ዜናቸዉ ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። የዓለም (የሰው) ሁሉ ደስታ የሆነ የመልአኩን ቃል ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ። ዓለምን ሁሉ የፈጠረ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

6፥ በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ። የሔዋን መድኃኒት ሆይ ደስ ይበልሽ። ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግበውን እሱን ጡትሽን አጥብተሽዋልና ደስ ይበልሽ። የሕያዋን (የጻድቃን) ሁሉ እናታቸዉ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ። ትለምኝልን ዘንድ ወደ አንቺ እናንጋጥጣለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

7፥ ድንግል ሆይ፥ ቅድስት ሆይ፥ ጌታን የወለድሽ ሆይ፥ እኛን ለማዳን ድንቅ ምሥጢር (ተዋሕዶ) በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዮ ልዮ መልክ የፈጠረ የእርሱን የገናንነቱን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

8፥ ወደ ደብረ ሲና የወረደ ለሙሴ ሕግን የሰጠ የተራራዉን ራስ በጽጋግ በጢስ በጨለማና በነፋስ የሸፈነ ፈርተው የቆሙትንም በነጋሪቶች ድምፅ የገሠጸ የአብ አካላዊ ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

9፥ በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ፣ ይኸዉም ወደ አንቺ የወረደዉ ነዉ። ሰውን የወደደ እርሱ ያለመለወጥ ባንቺ ሰው ሆነ። እንደ እኛ በሚናገር ሥጋ ፍጹም ሆኖ አምላክ በመንፈስ ቅዱስ በማኅፀንዋ አደረና ፍጹም ሰዉ ሆነ። አዳምን ያድነዉ ዘንድ፣ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘንድ። በሰማያት (በሰማያዊ መዓርግ) ያኖረው ዘንድ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

10፥ የድንግል ገናንነቷን ሊናገሩት አይቻልም። ጌታ መርጧታልና የሚቀርበዉ በሌለ ብርሃን ዉስጥ የሚኖር እርሱ መጥቶ አደረባት። ዘጠኝ ወር በማኅፀንዋ አደረ። የማይታይና የማይመረመር (ታይቶ የማይታወቅ) እርሱን በድንግልና ወለደችው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

11፥ ነቢዮ ዳንኤል ያየው ያለ እጅ ከረጅም ተራራ የተፈነቀለዉ ያ ደንጊያ ከአብ ዘንድ የወጣው ቃል ነዉና መጥቶ ያለ ወንድ ዘር ከድንግል ተወልዶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

12፥ እንደ ንጹሕ ጫፍ የሆንሽ የሃይማኖት መገኛ ነሽ ፣ የቀናች የቅዱሳን አባቶቻችን ሃይማኖታቸዉ ነሽ። አምላክን የወለድሽና በድንግልና የታተምሽ ንጽሕት ሆይ የአብን ቃል ወለድሽልን። ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን መጣ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

13፥ የከበርሽ ጌታን የወለድሽ ሆይ፣ የማይታይ ቃልን የተሸከምሽዉ የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ። እሱን ከወለድሽው በኋላ በድንግልና ኖረሻልና በፍጹም ምስጋና ያገኑሻል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

14፥ የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረዉን ነገር መናገር የሚቻለዉ ምን አንደበት ነዉ? ኪሩቤል ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፋኑ (ማደሪያዉ) ሆንሽ። የተከበርሽ ሆይ፥ እናመሰግንሻለን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ፣ ስምሽን በልጅ ልጅ እንጠራለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

15፥ እናትና አገልጋይ (ገረድ) ማርያም ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፣ የታቀፍሽዉን መላእክት ያመሰግኑታልና ኪሩቤልም በፍርሃት ይሰግዱለታልና፣ ሱራፌልም ያለማቋረጥ ክንፋቸውን ዘርግተው የሚመሰገን ንጉሥ (የክብር ባለቤት) ይህ ነዉ። በይቅርታው ብዛት የዓለምን ኃጠአት ያስተሠርይ ዘንድ የመጣዉ ይህ ነዉ ይላሉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ረቡዕ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

1፥ የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ፥ የሰማያት ሠራዊት (መላእክት) ንዕድ ነሽ ይላሉ፣ ድንግል ማርያም የምሥራቅ ደጅ ናት። ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት። አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘምና አንድ ልጁን ላከው በአንችም ሰው ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2፥ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ፥ ትውልድ ሁሉ አንቺን ብቻ ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር (ከተማ) ሆይ፥ ነቢያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ፣ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና። የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ ሕዝቡም (ሠራዊቶቻቸዉም) በብርሃንሽ ይሄዳሉ። ማርያም ሆይ፥ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል። ካንቺ ለተወለደዉም ይሰግዱለታል፣ ያገኑታልም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

3፥ የዝናም ዉሃ የታየብሽ የእውነት ደመና አንቺ ነሽ። አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይል ጋረደሽ። ማርያም ሆይ፥ ለዘለዓለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን ወለድሽልን መጥቶም ከኃጢአት አዳነን። ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ፥ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነዉ፣ ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርኸን ለድንግል ማርያም ፀጋን የተመላሽ ሆይ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነዉና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርካት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

4፥ ጸጋን አገኘሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይልም ጋረደሽ (ጸለለብሽ)። ማርያም ሆይ፥ በእውነት ቅዱስን ወለድሽ ዓለምን ሁሉ የሚያድን መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

5፥ አንደበታችን የድንግልን ሥራ ያመሰግናል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት አገር ከእርሷ ስለተወለደ አምላክን የወለደች ማርያምን ዛሬ እናመስግናት አሕዛብ ኑ ማርያምን እናመስግናት። እናትና ድንግልን (ሁለቱንም) ሆናለችና ርኵሰት የሌለብሽና የአብ ቃል መጥቶ ካንቺ ሰዉ የሆነ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ። ነውር የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ። ስለቀደመ ሰው አዳም ሁለተኛ አዳም የሆነ የክርስቶስ ማደሪያዉ የምትናገሪዉ ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ። ከአባቱ ያልተለየ አንድ እሱን የተሸከምሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። በክብር ጌጽ ሁሉ እርሱ መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንጽሕት የሠርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ። የመለኮት እሳት (ባሕርይ) ያላቃጠለሽ ዕፀ ጳጦስ ሆይ ደስ ይበልሽ። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠዉን ሰማያዊ (መለኮትን) በሥጋ የተሸከምሽ አገልጋይና (ገረድና) እናት ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ። ስለዚህ ንጹሓን ከሆኑ መላእክት ጋራ በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተን እናመስግን፣ በሰማይም ለእግዚአብሔር ምሥጋና ይሁን፣ በምድርም ዕርቅ ይሁን እንበል ክብርና ምሥጋና (ጌትነት) ያለው እርሱ አንቺን ወዷልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

6፥ ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፣ የአብን ቀል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማያት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማሕፀንዋ ተሸከመችው። ይህቺ ከኪሩቤል ትበልጣለች፣ ከሱራፌልም ትበልጣለች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና። የነቢያት ሀገራቸዉ ኢየሩሳሌም ይህች ናት፣ ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው። በቅዱሳን የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኖአልና፣ ኑ ይህን ድንቅ እዩ፣ ስለ ተገለጠልን ምሥጢር ምሥጋና አቅርቡ ሰው የማይሆን ሰው ሆኖዋልና ቃል ተዋሕዷልና። ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማይ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት (መለኮት) ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረዉ ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

7፥ ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እርሷ መሰከረ ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ ምሥራቅ አየሁ አለ። ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፥ ኆኅትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት፣ እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ ቀድሞው በድንግልና ኖራለችና። መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለድሽ ሆይ፥ የማኅፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፣ አንቺም ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ፣ የእውነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና። በምድር ላይ ከሚኖሩ ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ላንቺ ይገባል። የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ። ከሰው ጋርም ተመላለሰ። መሓሪ ይቅር ባይ ሰውንም ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ሐሙስ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

1፥ ርኵሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች፥ የአብ ቃል በርሷ ሰው ሆኖዋልና እሳተ መለኮቱ (የመለኮቱ ባሕርይ) አላቃጠላትምና። ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠምና፥ ሰው ቢሆን መለኮቱ አልተለወጠም። በእዉነት አምላክ ነውና በእውነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2፥ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ፥ ሁላችን እናገንሻለን። ይቅርታሽ ለሁላችን ይሆን ዘንድ ነውና። ሔዋን እንጨት በልታ ባደረገችው ዓመፅ በባሕሪያችን ያደረ የቀድሞው እርግማን በእርሷ የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። ስለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ። ዳግመኛ ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን። ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን። ይኸውም እኛን ስለ መዉደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክቡር ሥጋው ፣ ክቡር ደሙ ነው። ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረውን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለው ምን ልቡና ነው? መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማት የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር አንድ ብቻ የሆነ አምላክነቱ ሳይለወጥ ከዓለም በፊት የነበረ የአብ ቃል ከአብ ዘንድ መጥቶ ልዮ ከሆነች እናቱ ሰው ሆነ፥ ከወለደችው በኋላም ድንግልናዋ አልተለወጠም። ስለዚህም አምላክን የወለደች እንደሆነች ታወቀች። የእግዚአብሔር የጥበቡ ስፋት ምን ይጠልቅ? በጻዕር በምጥ በልብ ጋር ትወልድ ዘንድ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት መገኛ ሆነች፥ ከባሕርያችን እርግማንን የሚያፋልንንም ያለ ወንድ ዘር ወለደችልን። ስለዚህም ሰውን የምትወድ ሆይ ክብር ላንተ ይገባል፣ ቸርና የሰውነታችን መድኃኒትም ነህ እያልን እናመስግነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

3፥ ያለ ወንድ ዘር አምላክን የወለደች ድንግል የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይደንቅ? ለዮሴፍ የታየዉ መልአኩ "ከርሷ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደዉ ያለ መለወጥ ሰዉ የሚሆነዉ የእግዚአብሔር ቃል ነው" ብሎ መስክሯልና። ማርያም የዚህ ደስታ ዕጽፍ የሆነ እርሱን ወለደችው። መልአኩ "ልጅ ትወልጃለሽ፣ ስሙም አማኑኤል ይባላል አላት። ትርጓሜዉም ፣ እግዚአብሔር ከኛ ጋራ ሆነ ማለት ነው። ዳግመኛ ወገኖቹን ከኃጢአታቸዉ የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል። በችሎታው (በኃይሉ) ያድነን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለም ክብር ይግባዉና ሰው የሆነ እርሱን አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አውቀነዋልና። ልዮ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችው፥ ልደቱንም ዘር አልቀደመውም፣ በመወለዱም ድንግልናዋን አልተለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ፣ ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ሰገል ሰገዱለት አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት፣ ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነ ሞቱም ከርቤ አመጡለት። ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

4፥ ከአዳም ገጎን አንዲት ዐፅም መንሣት ምን ይደንቅ? ከርሱ ሴትን ፈጠረ፥ የሰው ፍጥረትንም ሁሉ ፈረ። ጌታ የአብ ቃል ተሰጠ ከልዩ ድንግልም ሰው ሆነና አማኑኤል ተባለ፣ ስለዚህ ሁል ጊዜ እርሷን እንለምን ከተወደደ ልጅዋ ታማልደን ዘንድ። በቅዱሳንና በሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ ዘንድ ቸር ናት ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋለችና፣ ለነቢያትም ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና፥ ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ሰማዕታትና ምእመናን የተጋደሉለት የጥበቡ ጸጋ ብዛት የማይታወቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዷል የይቅርታውን ብዛት መርምረን እንወቅ (እንፈልግ) መጥቶ አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

5፥ እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ ብሎ ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትም። ጻድቅ እርሱ (ዳዊት) ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ፥ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈጸመ። ከዚህም በኋላ እነሆ በኤፍራታ ሰማነዉ ብሎ በመንፈስ ቅዱስ አሰምቶ ተናገረ ይህቺዉም ፣ አማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወለድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት። ዳግመኛም ከነቢያት አንዱ ሚክያስ አንቺ የኤፍራታ ክፍል የሆንሽ ቤተ ልሔም ከይሁዳ ነገሥታት መሳፍንት ሀገር አታንሺም፥ ወገኖቼ እስራኤልን የሚጠብቃቸዉ ንጉሥ ካንቺ ይወጣልና። ከዛሬ ጅምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከቸር አባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ምሥጋና ስለተገባው ስለ ክርስቶስ በአንድ መንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተናገሩ የነዚህ የሚክያስና የዳዊት ነገር ምን ይረቅ? ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

6፥ ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ጠላቶቹ በተነሠሡበት ጊዜ ከቤተ ልሔም ምንጭ ዉኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ። የጭፍሮቹ አለቆች ፈጥነዉ ተነሱና በጠላቶቹ ከተማ ተዋግተው ሊጠጣ የወደደውን አመጡለት። ጻድቅ ዳዊት ግን ጨክነዉ ሰዉነታቸውን ስለ እርሱ ለጦርነት ለሞት አሳልፈው እንደሰጡ ባየ ጊዜ ያን ውኃ አፈሰሰ ከእሱም አልጠጣም። ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በዕዉነት ናቁ፣ ደማቸዉንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ። እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

7፥ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማሕፀን አደረ። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም እንደኛ ሰዉ ሆነ፣ ነቢያት ትንቢት እንደ ተናገሩለት በቤተ ልሔም ተወለደ። ፈጽሞ አዳነን ወገኖቹም አደረገን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ዓርብ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

1፥ ከሴቶች ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። የማሕፀንሽ ፍሬም የተባረከ ነው። ያለ ርኵሰት አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ፥ እዉነተኛ ፀሐይ ከአንቺ ወጣልን ጌታ ተወለደልን በክንፈ ረድኤቱም አቀረበን እርሱ ፈጥሮናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2፥አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ የብርሃን እናት ነሽና አንችን ብቻሽን በክብር በምስጋና እናገንሻለን። የተባረክሽ አንቺ ከመላእክት ትበልጫለሽ ከደቂቀ አዳምም ትበልጫለሽ። ገናንነትሽን መናገር የሚቻለዉ ማን ነዉ? አንችን የሚመስል የለምና።ማርያም ሆይ መላእክት ያገኑሻል። በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማህፀንሽ አድሯልና። ሰዉን የሚወድ ወደ እርሱ አቀረበን። ክብር ምስጋና ያለዉ እርሱ የእኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

3፥የደናግል መመኪያቸው አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ከዓለም በፊት የነበረ እርሱ ሰው ሆኖዋልና ከአንቺ ተወለደ፣ ሥጋችንን ነሣ (ተዋሐደ) መንፈስ ቅዱስንም ሰጠን በቸርነቱ ብዛት መሳዮቹ አደረገን። ጸጋንና ክብርን ከተቀበሉ ብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ። አምላክን የወለድሽ ማርያም ሆይ ልዑል እግዚአብሔር ያደረብሽ (የከተመብሽ) ረቂቅ ከተማ ነሽ በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ የሚኖረዉን ጌታን በመሐል እጅሽ ይዘሽዋልና። በቸርነቱ ብዛት ሥጋዊ ፈጥረትን ሁሉ የሚመግብ እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፣ ይኸውም ሁሉን የሚያድን አምላካችን ነው። ለዘላለሙ ይጠብቀናል እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ እርሱ ፈጥሮናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

4፥ ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውሃ ምንጭ ናት፣ የማሕፀንዋ ፍሬ ሰውን ሁሉ አድኗልና። ከእኛም እርግማንን አፋልን ፣ በመካከላችንም ሆኖ በመስቀሉ አስታረቀን በልዩ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛ ወደ ገነት መለሰው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፥ ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናት፣ ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት። ኀጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

6፥ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር። «መልአኩ ቅድስት ድንግል ሆይ፥ ሰላምታ ይገባሻል ብሎ አክብሮ ከነገረኝ ነገር በቀር ምንም ምን ሌላ የማውቀው እንደሌለኝ እግዚአብሔር ያውቃል´ አለች። የማይቻለውን ቻልሽ፣ የማይወሰነውንና ምንም ምን የሚወስነው የሌለውን ወሰንሽ። በክብር ሁሉ ላይ ጸጋን የተመላሽ ሆይ፥ ምሥጋናሽ ይበዛል ክብርሽም ፍጹም ነው፣ የአብ ቃል ማደሪያ ሆነሻልና። የክርስቲያን ወገኖች ምእመናንን የምትሰበስቢያቸውና ማሕየዊ የሚያድኑን ለሆኑ ሥላሴ ሰጊድን (መስገድን) የምታስተምሪላቸዉ ሰፊ መጋረጃ አንቺ ነሽ፥ ሙሴ ያየውን የእሳት ዐምድ የተሸከምሽ አንቺ ነሽ፥ ይኸውም መጥቶ በማሕፀንሽ ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ሰማይንና ምድርን ለፈጠረ ጌታ ማደሪያ ሆንሽ፣ ዘጠኝ ወር በማሕፀንሽ ተሸከምሽው፥ ሰማይና ምድር ለማይወስኑት የታመንሽ አንቺ ነሽ። ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ፣ ብርሃንሽ ከፀሓይ ብርሃን ይበልጣል። ቅዱሳን በፍጹም ደስታ ያዩት ኮከብ ካንቺ የተወለደ ምሥራቅ አንቺ ነሽ፣ ይኸውም በፃዕርና በምጥ ትወልድ ዘንድ በሔዋን የፈረደባት ነዉ። አንቺ ማርያም ግን ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ የሚል ቃልን ሰማሽና መጥቶ ያዳነን የፍጥረት ሁሉ ገዥ የሆነ ንጉሥን ወለድሽልን መሓሪ ነው ሰውንም ወዳጅ ነው። ስለዚህ ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ፣ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፥ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋራ ነውና ደስ ይበልሽ እያልን መልአኩ ገብርኤል እንዳመሰገነሽ እናመሰግንሻለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

የሶርያዉ ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰዉ ቅዳሜ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምሥጋና።

1፥ ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመኻል እጅሽ የያዝሽዉ ሆይ በሁሉ የተቀደስሽ ነሽ። ፍጥረቱ ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልን እያሉ ከአንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

2፥ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፥ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፥ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነዉና ደስ ይበልሽ። ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ ገናንነትሽን እናመሰግናለን (እናደንቃለን) ፣ እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምሥጋናን እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን ከማኅፀንሽ ፍሬ ተገኝቷልና። ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አቀረበን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

3፥ እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና የልዑል ኃይልም ጸልሎሻልና። ማርያም ሆይ፥ ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶም ከኃጢአት ያዳነን የአብ ልጅ ቃልን በእውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

4፥ ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ የተወለደ ከዓለም በፊት የነበረ አንዱ ቃል ራሱን (ባሕርዩን) ሰወረ ካንቺም የተገዥን (የሰዉን) አርኣያ ነሣ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

5፥ አምላክን ያለርኵሰት የወለድሽው ሆይ፥ የምድር ሁለተኛ ሰማይን ሆንሽ እውነተኛ ፀሓይ ካንቺ ወጥቶልናልና እንደ ነቢያት ትንቢትም ያለ ዘርና ያለ መለወጥ ወለድሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

7፥ የንጉሥ ክርስቶስ እናቱ ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ በሆነ ምሥጢር (ተዋሕዶ/) አማኑኤልን ወለድሽው። ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ፣ ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

8፥ እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ፣ በሁሉ በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት ማኅፀንሽ ተሸክመሽዋልና። እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰዉ በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ ሆንሽን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

9፥ የተባረክሽና ንጽሕት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ፥ እነሆ ጌታ የፈረዉን ዓለም ሁሉ በይቅርታዉ ብዛት ያድን ዘንድ ካንች ወጣ (ተወለደ)። ፈጽመን እናመሥግነው ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

10፥ ያለ ርኵሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ የዓለም ሁሉ መክበሪያ ንጽሕት ጽዋዕ ነሽ፣ የማትጠፊ ፋና ነሽ፣ የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ፣ የቅዱሳን መደገፊያቸዉ (መጠጊያቸዉ) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ፣ ቸር አዳኛችን ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን፣ ፈጽሞ ይቅር ይለንና ይምረን ዘንድ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ይዌድስዋ

ይዌድስዋ መላእክት መላእክት ማርያምን በመንጦላዕት ውስጥ ያመሰግኗታል፣ ሓዳስ ጣዕዋ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል እያሉ፣ መላእክ ማርያምን ቃልን ተቀበዪው አላት ካንቺ ዘንድ ይመጣልና በማህጸንሽም ያድራል እንዴት ከድሃ ቤት አደረ እንደ ምስኪን ከሰማያት ወርዶ የርሷን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ ተወለደ፡፡

በ፮ ኛው ወር ገብርኤል መልአክ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ተላከ ካንዲት አገር ናዝሬት ገሊላ ከምትባል ለዮሴፍ እጮኛ ከሆነች ከድንግል ዘንድ የዚች የድንግል ስሟ ማርያም ነው፡፡ መልአክ ወደ እርሷ ገብቶ እንዲህ አላት ደሰታ ይገባሻል እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ሰው ሆኗልና ከሴቶች ይልቅ አንቺ ቡርክት ነሽ ፡፡ ከቃሉ አነጋገር አይታ ደነገጠች እንዲህም አለች እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ ይደረግልኛል? መልአክ እንዲህ አላት ማርያም ሆይ አትፍሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ፡፡ እነሆ ትፀንሺያለሽ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ ፡፡ እርሱም ታላቅ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የዳዊት የአባቱን ዙፋን ይሰጠዋል፡፡ እርሱም በያዕቆብ ወገን ለዘለዓለሙ ይነግሣል መንግሥቱም አያልፍም ፡፡ ማርያም መልአኩን እንዲህ አለችው ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል? እንዘ ኢየአምር ብእሴ መልአኩም እንዲህ አላት መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው፡፡ እነሆ ኤልሳቤጥ ካንቺ ወገን የምትሆን ከሸመገለች ካረጀች በኋላ ፀነሰች ልጅም አገኘች እነሆም ይህ ስድስት ወር ሆነ መካን ሲሏት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ማርያም መልአኩን እንደ ቃልህ ይደረግልኝ እኔ የእግዚአብሔር ባርያው ነኝ አለችው ፡፡

መልአኩ ገብርኤል ማርያም ድንግል ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል አላት ፣ ወላዲተ አምላክ ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ ቅድስት ነሽና ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ የመለኮት ማደሪያ ነሽና ፣ ምስጋና ይገበሻል፡፡ የተሸለመች ድንኳን ነሽና ፣ ምስጋና ይገበሻል፡፡ የመላእክት እኅት የሕዝቡ ሁሉ እናት ነሽና ፣ ምስጋና ይገበሻል ፡፡ የሁሉ እመቤት ማርያም ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ የሰላም እናት ማርያም ምስጋና ይገባሻል፡፡ ልዑል ማደሪያው ትሆኚ ዘንድ መርጦሻልና ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሸለሙ ፣ ላንቺ ምስጋና ይገበሻል፡፡ የምስራቅ ደጃፍ የብርሃን እናቱ ላንቺ ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ ከፀሐይ ፯ እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ላንቺ ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ ማርያም ሆይ ከተመረጡ የተመረጥሽ ከተከበሩ የተከበርሽ ላንቺ ፣ ምስጋና ይገባሻል፡፡ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ፣ ያድነን ዘንድ በአባቱ ምስጋና ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር በመጣ፣ ጊዜ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥአንን በግራው ባቆመ ጊዜ፣ እኛን ከሰማዕቱ እስጢፋኖስ ከመጥምቁ ዮሐንስ ጋር ከሁሉ ቅዱሳን ሰማዕታት ጋር ያቆመን ዘንድ፣ ለምኝልን ለዓለመ ዓለም አሜን ለዘለዓለሙ ይቅር ይበለን አሜን !!!