በጎ መዓዛዬ ሽታዬ ነሽ በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ ባንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ ምሳሌ የሌለሽ ነይ እመቤቴ ዘመዴ ነሽ ነይ እመቤቴ ያን ክፉ ዘመን ነይ እመቤቴ ያለፍኩብሽ ነይ እመቤቴ በፍቅርሽ እሳት ነይ እመቤቴ ልቤ ነደደ ነይ እመቤቴ እናትነትሽን ነይ እመቤቴ ስለወደደ ነይ እመቤቴ የሰውስ ጉልበት ነይ እመቤቴ ምን ይረባኛል ነይ እመቤቴ ሰረገላዬ ነይ እመቤቴ መች ያድነኛል ነይ እመቤቴ ከተሰወረ ነይ እመቤቴ ክፉ መከራ ነይ እመቤቴ እድናለሁኝ ነይ እመቤቴ አንቺን ስጠራ ነይ እመቤቴ ለስንፍናዬስ ነይ እመቤቴ መቼ ልክ አለው ነይ እመቤቴ ስለበደሌ ነይ እመቤቴ እተክዛለሁ ነይ እመቤቴ ላነጋገሬ ነይ እመቤቴ ማጣፈጫ ነሽ ነይ እመቤቴ ተሰምቻለሁ ነይ እመቤቴ ድንግል ሆይ ስልሽ ነይ እመቤቴ ለመንገዴ ስንቅ ነይ እመቤቴ የረሃቤ መርሻ ነይ እመቤቴ ለታመመ ሰው ነይ እመቤቴ ነሽ መፈወሻ ነይ እመቤቴ የተማጸነ ነይ እመቤቴ በስምሽ አምኖ ነይ እመቤቴ ማን አፍሮ ያውቃል ነይ እመቤቴ ፊትሽ ለምኖ ነይ እመቤቴ