ዕፁብ ድንቅ ነው ውለታው እግዚአብሔር ለኛ ያደረገው ከቶ አይጥለንም ለዘለዓለም እንደ አምላካችን ማንም የለም ወድቀን ነበረ ተነሥተናል ባሕር አቋርጦ አሻግሮናል ደንቅ አደረገ ተአምር ሠራ እያንሳፈፈ ያንን ተራራማውጫ እፁብ ድንቅ ነው ውለታው እግዚአብሔር ለኛ ያደረገው ከቶ አይጥለንም ለዘለዓለም እንደ አምላካችን ማንም የለም የጠፋውን በግ የፈለገ እራሱን ባዶ አደረገ መስቀል ታቅፎ ክንዱ ዛለ ምን ያልሆነልን ነገር አለ እፁብ ድንቅ ነው ውለታው እግዚአብሔር ለኛ ያደረገው ከቶ አይጥለንም ለዘለዓለም እንደ አምላካችን ማንም የለም ከአባትም በላይ አባት ነው የልጆቹ አንባ የሚገደው የጭንቀታችን ተካፋይ አዛኝ ጌታ ነው ሁሉን ቻይ እፁብ ድንቅ ነው ውለታው እግዚአብሔር ለኛ ያደረገው ከቶ አይጥለንም ለዘለዓለም እንደ አምላካችን ማንም የለም ዳግም እንድንቆም በሕይወት ፈጽሞ ወደደን እስከሞት ከእንግዲህ አንፈራም እንጸናለን ለክፉ የማይሰጥ አባት አለን