በኀዘኔ በችግሬ መጽናኛዬ ነሽ ረዳቴ እመ አምላክ አደራ ድንግል እመቤቴ ለዓለም ተዘርግቶ እጄ ባዶ ሆኗል የራሴ ላይ አክሊል ተሽቀንጥሮ ወድቋል ከኤልዛቤል ሸሽቼ መጣሁኝ ወደ አንቺ የጎሰቆልኩትን እኔን ተመልከቺ በኀዘኔ በችግሬ መጽናኛዬ ነሽ ረዳቴ እመ አምላክ አደራ ድንግል እመቤቴ የእግሬ መሰናከል ለዓለም ደስታ ነው ተስፋ ቢስ መሆኔ ለጠላቴ ድል ነው የደስታ መፍሰሻ የኤልሳቤጥ ዘመድ እንዳልሰናከል ምሪኝ በመንገድ በኀዘኔ በችግሬ መጽናኛዬ ነሽ ረዳቴ እመ አምላክ አደራ ድንግል እመቤቴ ምድር ትለኛለች ተስፋቢስ ብቸኛ ሳለቅስ ሳነባ አይታኛለችና ከቤተመቅደሱ ለኔስ ዘመድ አለኝ በኀዘኔ ሰዓት አለሁ የምትለኝ በኀዘኔ በችግሬ መጽናኛዬ ነሽ ረዳቴ እመ አምላክ አደራ ድንግል እመቤቴ ከአመድ የወደቀ ትንሽ ገንዘብ አለኝ ልብሽ ራርቶልኝ ፈልጊኝ አጥብቀሽ እምነቴ እንዳይደክም አንዳልጠፋ ልጅሽ አድጌአለሁ እና ከደጀ ሰላምሽ