የኀዘኔ ደራሽ ነሽ የጭንቀቴ የችግሬ ደራሽ ነሽ የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል/2/ መልካሚቱ ርግብ ድንግል እመቤቴ ማርያም እናቴ ነሽ ድንግል እመቤቴ ከፍጥረታት ሁሉ ድንግል እመቤቴ ገናና ነው ክብረሽ ድንግል እመቤቴ የኀዘኔ መጽናኛ ድንግል እመቤቴ እንባዬን አባሽ ነሽ ድንግል እመቤቴ የኀዘኔ ደራሽ ነሽ የጭንቀቴ የችግሬ ደራሽ ነሽ የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል/2/ ዋሻ መጠለያ ድንግል እመቤቴ የዘለዓለም ቤቴ ድንግል እመቤቴ መንገድ ስሄድ ስንቄ ድንግል እመቤቴ መጠጤ ነሽ ምግቤ ድንግል እመቤቴ እመ አምላክ ስጠራሽ ድንግል እመቤቴ ይጠፋል ረሀቤ ድንግል እመቤቴ የኀዘኔ ደራሽ ነሽ የጭንቀቴ የችግሬ ደራሽ ነሽ የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል/2/ የእናትነትሽን ድንግል እመቤቴ ፍቅርሽን አየሁት ድንግል እመቤቴ ጎጆዬን ስትሞይው ድንግል እመቤቴ ባዶ የሆነውን ድንግል እመቤቴ አንቺ እያለሽልኝ ድንግል እመቤቴ ምን እሆናለሁኝ ድንግል እመቤቴ