ኪዳነ ምሕረት እመቤት የዓለም ሁሉ መድሃኒት ቅድስተ ቅዱሳን ንጽሕት አንቺ ነሽ የአምላካችን እናት ጌታ አንቺን መረጠሽ ልዩ አድርጎ በሚያስድንቅ ሚሥጢሩ ተዋሕዶ ለልዑል ማደርያነት የተመረጥሽ ያለህማም ወለድሽው ድንግል ሆነሽ እናትነት ድንግልና አስተባበረሽ ይዘሻልና ድንግልም እናትም እመብርሃን ቅድስተ ቅዱሳን እኛን አማልጅን