ጸጋ የተሰጠህ የምህረት መላክ ሚካኤል እርዳን ስንጨነቅ ስንሰደድ ስንጣል አትለየን በግዞት መሃል ከግብፅ ባርነት መርተህ አዉጥተኸናል ምልጃህ ለዘወትር ሲያጽናናን ይኖራል ቀይ ባህር ተከፍሎ በድል ተሻግረናል የሚካኤል አምላክ እኛን ረድቶናል። ጸጋን የተሰጠህ የምህረት መላክ ሚካኤል እርዳን ስንጨነቅ ስንሰደድ ስንጣል አትለየን በግዞት መሃል ያዕቆብን የጠበቅህ ሩኅሩሁ መልአክ የኢያሱ ረዳት ሚካኤል አንተ ነህ ዛሬም ለሚጠሩህ ፈጥነህ ትደርሳለህ ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ተአምር አለህ። ጸጋ የተሰጠህ የምህረት መላክ ሚካኤል እርዳን ስንጨነቅ ስንሰደድ ስንጣል አትለየን በግዞት መሃል በምሕረት ዐይኖችህ ሁሌ ተከተለን ጨለማው ልባችን ብሩህ ይሁንልን የለመነህ ሁሉ ምኞቱ ተሳክቷል ሚካኤል ሆይ ብሎ ማንስ አፍሮ ያውቃል!!!