እንደቸርነትህ አቤቱ ማረን /2/ አንደምሕረትህ ይቅርታን ስጠን /2/ ከኃጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ /2/ ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ /2/ እኔም አመጻዬን በደሌን ሳውቀው /2/ ፍጹም የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው /2/ አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ /2/ አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ /2/ ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን /2/ መውደቄን ተመልከት አምላክ ብርሃን /2/ አሁን ተባርክ ዘንድ ማህበራችንን ሀገራችንን ጌታ ሆይ ላክልን መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስን