ምስጋና ነዉ ሥራዬ በዘመኔ በዕድሜዬ ለዋለልኝ ውለታ ምን ልክፈለው ለጌታ ትናንትና ጥልቁ ነበረ መኖሪያዬ የማዳኑ ቀን ደረሰ የጌታዬ እራቁቴን ሸፍኖኛል በብርሃኑ ምግቤ ሆኗል ስሙን ማወደስ በየቀኑ ምስጋና ነዉ ሥራዬ በዘመኔ በዕድሜዬ ለዋለልኝ ውለታ ምን ልክፈለው ለጌታ አልተራብኩም አልተጠማሁም በዘመኔ ምግበ ስጋ ምግበ ነፍስ ነው ጌታ ለኔ ተበጥሷል የሳቱ ገመድ ሰንሰለት አልረሳሁም የእርሱን ውለታ ብድራት ምስጋና ነዉ ሥራዬ በዘመኔ በዕድሜዬ ለዋለልኝ ውለታ ምን ልክፈለው ለጌታ ማን ያፈቅራል እስከሞት ድረስ ዋጋ ከፍሎ ማን ያድናል ባለሥልጣኑን ሞትን ገድሎ አማኑኤል በፍቅሩ ፀዳል ምድርን ከድኖ ሰው አርጎኛል የማይሆኑትን ሁሉን ሆኖ ምስጋና ነዉ ሥራዬ በዘመኔ በዕድሜዬ ለዋለልኝ ውለታ ምን ልክፈለው ለጌታ እንዴት ሆኜ ፍቅሩን ልግለፀው እንዴት ብዬ ስለ እጆቹ በእንባ ጨቀየ መኝታዬ በእርሱ ቁስል ነፍሴ ወጥታለች ከመከራ በምስጋና ስሙን ማክበር ነው የኔ ስራ።