የሕይወቴ መታመኛ የነፍሴ ተስፋ ጌታዬ አምላኬ መድኃኔዓለም ላመስግንህ እቀኛለሁ ለውዳሴህ (2) መላእክትም ከሰማያት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተነህ እያሉ በጸናጽል አሸብበው ይጠሩሃል በዝማሬያቸው(2) ኧኸ ቅዱስ ዳዊት በበገና ከእስራኤል ሀገር (2) በተመስጦ ጽርሐ አርያም ገብቶ ዘመረልህ አንተነትህን አውቆ(2) ኧኸ ሕፃናት አንተን አምነው በአህያ ተቀምጠህ ስትመጣ (2) አፍ አውጥተው አመሰገኑህ ሆሣዕና በአርያም አሉ (2) ኧኸ ሃሌ አለ ቅዱስ ዳዊት ጸናጽል መቋሚያ አንሥቶ (2) ምስጋናህን በልቡ ሽቶ በመንፈስም በአንተ ተመርቶ (2) ኧኸ ፈለጉንም ተከትለው ካህናት በሙሉ ቆመው(2) ይቀኛሉ ለቅዱስ ስምህ በማኅሌት በመመስገኛው (2) ኧኸ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያመስግንህ አንተን(2) ከልብ ሁነው በንጹሕ እምነት እንደ ዕዝራ አንደ ዳዊት (2) ኧኸ