ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ ለኛ እስከ ሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት(2) ሞትን የረገጠ ልጅሽ ከአንቺ ጋር ነው ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል ትንሣኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኀይል ያገኛል(2) ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ ለኛ እስከ ሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት(2) ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር ለምን ተሠወረን የትንሣኤሽ ምስጢር በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኀይል ያገኛል(2) ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ ለኛ እስከ ሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት(2) መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትወርጂም ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኀይል ያገኛል(2) ድንግል ትንሣኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ ለኛ እስከ ሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምሕረት(2) ቶማስ ከደመና ወርዶ ሲያናግረን ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምሕረት ሞትማ በሞት ተሸንፏል በአንቺ ላይ እንዴት ኀይል ያገኛል(2)