ከጨለማው ገዢ ከጽልመቱ ንጉሥ ከኃጢአት ባርነት ላዳነን ክርስቶስ በመገረፉ ቁስል ፈውስን ለቸረን ታላቅ ምሕረቱን ሞቶ ላደለን ለመድኃኔዓለም ውዳሴ አለን በእልልታ በሽበሸባ እንዘምራለን ኧኸ በእልልታ በጭብጨባ እንዘምራለን እስር ቤቱ ይፍረስ ትናወጥ ምድሪቱ የእግር ብረት እስር ይርገፍ ሰንሰለቱ የኃጢአት እስረኞች ይውጡ በነፃነት የአምላክን ሥራ ዐይናቸው ይመልከት ለመድኃኔዓለም ውዳሴ አለን በእልልታ በሽበሸባ እንዘምራለን ኧኸ በእልልታ በጭብጨባ እንዘምራለን እንዘምር ለጌታ በሩ እንዲከፈት በመዝሙር ይናወጥ የወህኒው መሠረት ዲያብሎስ ይደንግጥ መጋረጃው ይውደቅ በአምላካችን ኃይል በግርማው ይጨነቅ ለመድኃኔዓለም ውዳሴ አለን በእልልታ በሽበሸባ እንዘምራለን ኧኸ በእልልታ በጭብጨባ እንዘምራለን እንመሰክራለን አምላክ ያንተን ሥራ ጸንቷል በልባችን የመስቀሉ አሻራ በፊቱ እንወድቃለን በምጋና ደምቀን የከንፈርን ፍሬ ተቀበል እያልን ለመድኃኔዓለም ውዳሴ አለን በእልልታ በሽበሸባ እንዘምራለን ኧኸ በእልልታ በጭብጨባ እንዘምራለን በቅዱስ አጠራር አምላክ የጠራችሁ እርሱ ዝቅ ብሎ ከፍ ያደረጋችሁ ክብሩ ሳይገባን በቤቱ ላቆመን ለታደገን ጌታ እንዘምር ተነሥተን ለመድኃኔዓለም ውዳሴ አለን በእልልታ በሽበሸባ እንዘምራለን ኧኸ በእልልታ በጭብጨባ እንዘምራለን