ለጥያቄዬ መልስ ሳላጣሁ መጣሁከደጅሽ ሱባዔ ገባሁ ማን አፍሮ ያውቃል በአንቺ ለምኖ በኪዳንኪ ተማህጸኖ ለነፍሴ ዕረፍቷ ታዛ መጠጊያ ካንቺ ተገኝቷል የሞቴ መውጊያ በሰላምታሽ ድምፅ ተባርኳል ቤቴ የጌታዬ እናት ለእኔም እናቴ ማርያም ኵኒ ለሕይወትየ ጸወኖ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ ቀንን ስናፍቅ በሌሊት ሆኜ አላተረፍኩም በሰው ታምኜ ለቁልፉ ልጅሽ ነው ለቋጠሮዬ አሳስሰሽልኝ አልፏል ሥቃዬ ኪዳነምሕረት ኵኒ ለልቡናዬ ብርሃኖ እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ ጉልበቴ ዝሎ ቀልዬ ሳለሁ በኪዳን ጥላሽ ተስፋ አግኝቻለሁ ደጅሽ መጥቼ ኃይሌ ታደሰ ያሳዳጆቼ ምክር ፈረሰ ወላዲተ አምላክ ኵኒ ለእርቃንዬ ክዳኖ እስመ ተማህጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ በሥዕልኪ ሥዕለ አድኅኖ ንሰግድ ለኪ የዝናቡ ምንጭ ፈጣን ደመና ከሴቶች ሁሉ ክብርሽ ገናና አንድያ ልጅሽ ወይን አድርጎኛል ከትላንት ይልቅ ዛሬ ባርኮኛል