የሉም ሞተዋል ሲሉን ኖረን የሉም ጠፍተዋል ሲሉን በዝተን አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን አለን በጌታ ሁሉን አልፈን (2) ለካስ ሰው ስለሮጠ አይቀድምም ጉልበታም ስለታገለ አይጥልም ጎልያድ ወድቋል በዳዊት ጠጠር የእኛ አምላክ ስሙ ከፍ ይበል ይክበር እግዚአብሔር ስሙ ከፍ ይበል ይክበር ጨክነን እኛ ሰይፉን ባንመዝዝም በእጃችን ጦር ጎመድን ባንይዝም ይዋጋል ዝም አይልም እግዚአብሔር ልጆቹን ፈጥሮ አይሰጥም ለፍጡር(2) በሚነድ እሳት መሐል ሆነን አልሞትንም ዛሬም በሕይወት አልን ያልሰማ ሁሉ ይስማ ይግረመው ያመለክነው እግዚአብሔር እንዲህ ነው(2) አሕዛብ ዝክራችንን ሊያጠፉ ቢደክሙ ብዙ ዘመን ቢለፉ ከአሸናፊዎች ሁሉ በልጠን አልሞትንም ዛሬም አለን በዝተን