እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋለ ባደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ የሀሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድነው ከቃሉ እብለትን ባያገኙበትም ዝምታውን አይተው አላዘኑለትም ባላወቁት መጠን ጠሉት ካለበደል ጥፋቱ ምን ይሆን የሚያደርስ ከመስቀል/2/ እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋለ ባደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ የሀሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድነው የልቡን ትህትና ፍቅሩን ሳያስተውሉ ቸሩ ጌታችንን አቻኩለው ሰቀሉ እሩህሩሁን ጌታ ቸንክረው ሰቀሉት ሞትን አስውግዶ ቢሰጣቸው ህይወት/2/ እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋለ ባደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ የሀሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድነው ስለ ቸርነቱ ስድብን ከፈሉት ስለ ርህራሄው የሾህ አክሊል ሰጡት ሀሞትና ከርቤ ሆምጣጤ ደባልቀው መራራ አስጎነጩት ጨክኖልባቸው/2/ እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋለ ባደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ የሀሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድነው ፈውስን ለሰጣቸው ልባቸውን ሞልተው አሉት ወንበዴ ነው ስቀለው ስቀለው ከጁ በረከትን የተሻሙ ሁሉ ይጮሁ ነበረ ይገደል እያሉ/2/