ነቢዩ ዳንኤል በጾም ስላመነ /2/ ከአንበሶች ጉድጓድ ሕይወቱን አዳነ/2/ ኤልያስ የወጣ በእሳት ሠረገላ /2/ በጾም በጸሎት ነው አይደለም በሌላ/2/ የነፍስንም ቁስል ጾም ድናለች /2/ የሥጋን ፍላጎት እያደከመች /2/ እስቲ ልብ እናድርግ እናስተውል ደግሞ/2/ ጌ ለሐዋርያት ያላቸውን ቀድሞ /2/ ይህ ርኩስ መንፈስ ሊወጣ የሚችል/2/ በጾም በጸሎት ነው እንደ ወንጌሉ ቃል /2/