colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

የተዘጋች መቅደስ

ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ የተዘጋች መቅደስ ንጽሕት አዳራሽ ሕዝቅኤል ያየሽ የምሥራቋ በር ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር የልዑል ማደሪያ አማናዊት መቅደስ ስለ ንጽሕናሽ ምስጋናን እናድርስ አዝ . . . ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል ማኅደረ መለኮት ወላዲተ ቃል ያለ ዘርዓ ብእሲ በኅቱም ድንግልና አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና አዝ . . . ምሥራቀ ምሥራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ ጨረቃን የምትመስይ ፀሐይን የወለድሽ የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምታሳሺ ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሽሺ አዝ . . .