colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ቀስተ ደመናው

የኖ ቃል ኪዳኑ ምልክት ዓርማው የመዳኑ ምሥጢር የሰላም ተስፋው እመቤቴ አንቺ ነሽ ቀስተ ደመናው (2) አንቺ የአሮን በትር ሳይተክሏት ያደገች የማክሰኞ እርሻ ያለዘር ያፈራች የሲና ሐመልማል የተዋሕዶ ምሥጢር ክብርት እመቤቴ ሀገረ እግዚአብሔር (2) አዝ . . . ዳዊት መሰንቆ የያሬድ ጸናጽል የደኝሞች ምርኩዝ የሰሎሞን አክሊል ሰላሜ ተስፋዬ የሐዘኔ ደራሽ የጽዮን ተራራ መሸሸጊያዬ ነሽ (2) አዝ . . . የኤልሳዕ ማሰሮ ጨው የተገኘብሽ የሕዝቅኤል ራእይ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ የአዳም ተስፋ የመዳኑ ብሥራት አንቀጸ ብርሃን ነሽ የአማኑኤል እናት(2) አዝ . . .