ድንግል ማርያም የወርቅ መሰላል ነሽ መሰላል ነሽ የወርቅ መሰላል ነሽ ሰውና አምላክን ያገናኘሽ አባ ችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ /2/ አሸልቦት እንቅልፍ ተኝቶ ከጠ?ዛ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላል ምሳሌሽን አየን ማርያም ድንግል አዝ . . . መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ከሰማይ /2/ እንደ ያዕቆብ ተኝቶ መንገድ ላይ ተስፋ አድርጎ ሲኖር የሰላሙን ዘመን ይኸው ተፈጸመ በአንቺ በእና ችን አዝ . . . በአንቺና በልጅሽ ሆነልን ሰላም /2/ በአንቺ ተፈጸመ የያዕቆብ ሕልም ሰውና መላዕክት ተለያይተው ሲኖሩ በልጅሽ መወለድ በአንድ ላይ ዘመሩ አዝ . . .