እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሸን የሕይወት እንጀራ አመጣሽልን በአሥራትም በአደራ ለአንቺ ተሰጠን አዝ . . . የኤልሳቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ የኃጢአ ችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ ምሥራችን ደስ ይዘሽልን መጣሽ ማርያም ስንልሽ ደረሽልን ፈጥነሽ አዝ . . . ውለ ሽ ብዙ ነው ከልብ የማይጠፋ ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ በእንተ ማርያም ብሎ ለለመነ የሰማይ የምድሩም ማንም አልጨከነ አዝ . . . በትራችን አንቺ ነሽ የምትደግፊን ባሕረ እሳትን የም ሳልፊን ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማ ደረ መለኮት ሁል ጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽእት አዝ . . .