አማን በአማን /4/ አማኑኤል ተመስገን ለዚህ ፍቅር ምን ልክፈልህ /2/ ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው እንደሰው በደል ቢቆጥር ጌ ለእኔስ ኃጢአት የለውም ቦ አዝ --- በየደቂቃው ኃጢአት ስሠራ ስሠርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም አዝ --- የኃጢአት ጉካ ጣፋጭ ቢመስልም ውጠ?ቱ መርሮ ፍጹም አይጥምም እንደበደሌ ስላልከፈልከኝ ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ አዝ ---