ምንተኑ አአስየኪ እሴተ በእንተ ከኲሉ ዘገበርኪ ሊተ /2/ የቅዱሳን ተስፋ የትንቢት ምዕራፍ የስደተኞች ስንቅ የምሕረት ደጃፍ የፍጥረት መመኪያ ምክንያተ ድኂን ለእኔም ለመንገዴ ስለሆንሽኝ ብርሃን አዝ . . . የዓለም ኑሮ ማርኮኝ ልቤ ሲዋልል በፈተናው ብዛት በሕይወት ስዝል ለሥጋዬ ፈቃድ ከቶ ስላልተውሽኝ ለነፍሴም ሰላምን ስላስገኘሽልኝ አዝ . . . በኃጢአት መጎስቆሌን ድካሜን ሳ ዪ በሐዘን በችግሬ ከእኔ ሳትለዪ ከመከራ አዘቅት በአንቺ ስለወጣሁ ለብዙ ውለ ሽ ምን እከፍልሻለሁ አዝ . . . የአዝማቹ ትርጉም: ስላደረግሽልኝ ሁሉ ምን እከፍልሻለሁ ማለት ነው።