ምስጋና ለስምሽ ድንግል እመቤቴ በአንቺ አማላጅነት ድ ነት በማግኘቴ ቅዱሳን አባቶች ቀንም ከሌሊት ለአንቺ ይቀኛሉ እንዲህ በማለት ከሀገረ ብህንሳ ፍቅርሽ አስገድዶት የአንቺ ንጽሕና ፍጹም አስደንቆት አባ ሕርያቆስ ተሞልቶ በመንፈስ ድንግል ሆይ አለ አንቺን ለማወደስ አዝ . . . ፋራን የተሰኘሽ የዕንባቆም ተራራ በረከት የሞላሽ የገነት አዝመራ ዕፀ ጳጦስ የተባልሽ የሙሴ ጽላት የይስሐቅ መዓዛ የአብርሃም ደግነት አዝ . . . እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ በቀኝ ትቆማለች አምራ ንግሥቲቱ ባለገንዘቦችም አሕዛብ በሙሉ ለክብርሽ ዝቅ ብለው ለአንቺ ይሰግዳሉ አዝ . . . ዓለም የዳነብሽ አንቺ የኖ መርከብ ምስጋናሽ መብዛቱ እንደሰማይ ኮከብ 12 ዘወትር ሁልጊዜ ቢሰላ ቢወራ ድንግል ሆይ አያልቅም የአንቺ ድንቅ ሥራ አዝ . . .