እዘኝልን ድንግል የአምላክ መንበር ዓለሙን በማየት ወድቀን እንዳንቀር /2/ በኃጢአት በበደል ከልጅሽ ለራቅን በዝሙት በሀሜት ዛሬም ለወደቅን በዲያብሎስ ተንኮል ለተተበተብን በአማላጅነትሽ ዛሬም ተማፀኚ ከኢየሱስ ክርስቶስ ምሕረትን ለምኚ /2/ በንስሃ ጥበን በፍቅሩ ተስበን ከልጅሽ እግር ስር ለመቀመጥ አብቂን /2/ በፈፀምነው በደል ተፀፃች አድርጊን መራራ እንባ እናፍስ ልብን መልሽልን /2/ ፈቃደ ሥጋና ፈቃደ ሰይጣን ዓለም ተደርባ ስ ስጨንቀን /3/ ሰላምን ተጠምተን ስንንከራተት ድንግል ድረሽልን የአምላክ እናት /2/ እባክሽ አትለይን እስከመጨረሻው እየቀረበ ነው የክርስቶስ መምጫው /2/ ድንግል ማርያም ሆይ እባክሽ አሳስቢ ለጻድቃን አይደለም ለኃጥአን ብለሽ /2/ በቀኝ እንዲያቆመን በዳግም ምጽአቱ ድንግል ለምኝልን ለአምላክ እናቱ ድንግል ለምኝልን ለአምላክ ወላዲቱ ቡሩኝን ልጆኟ ብሎ እንዲቀበለን ፍቅሩን ቸርነቱን አስቦ እንዲምረን /3/ ድንግል አደራሽን ስለኛ አሳስቢልን በእርሱ መሠረት ላይ ክርስቶስ ያቁመን /2/