የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት ድንግልን ከመሐል ሚካኤልን ከፊት አእላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት እዪት ተመልከቱት የሰማዪን ድምቀት /2/ የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት ኝህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ ይህን ልዩ ክብር ሊያዪ የ ደሉ በጽድቅ ሥራቸው ደምቀው ይ ያሉ /2/ አዝ . . . የቅዱሳን ሕብረት የቅዱሳን ሀገር ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር ጽድቅና ርህራሄ የተሞላ ሰማይ እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ /3/ አዝ . . .