ሃሌ ሉያ ለእርሱ እንዘምር በእልል ክብር ይገባዋል የሠራዊት ጌ /4/ ጸናጽል ከበሮ በገናም ይደርደር ነፃ ላደረገን ከባርነት ቀንበር /4/ ለፍቅር ለሰላም ለምሕረት አባት ይጎሰም ነጋሪት ይነፋ መለከት /4/ ሁሉ በእጁ ሳለ ድሃ ለሆነልን የነገሥ ት ንጉሥ ጌ ችን ይመስገን /4/ ለገዛልን ርስት በደሙ ለዋጀን በመስቀል ተሰቅሎ በሞቱ ላዳነን /4/ ስለኛ ደህንነት ሐፍረትን ለናቀው ለአማልክት አምላክ ምስጋና ይድረሰው /4/ እኛ ክርስቲያኖች ሁላችንም ዛሬ ለዓለም መድኃኒት እናቀርብ ዝማሬ /4/ ሃሌ ሉያ ለእርሱ እንዘምር በእልል ክብር ይገባዋል ለሠራዊት ጌ /4/ ፀናፅል ከበሮ በገናም ይደርደር ነፃ ላደረገን ከባርነት ቀንበር /4/