ኃይሉን ያለብሰኛል ቅዱሱ ጌ ዬ የዓይኖኟ ተስፋ ማኝ ጠባቂዬ በሰላም ወጥኟ በሰላም እገባለሁ እግዚአብሔር ሳለልኝ ምንስ እሆናለሁ /2/ በእርሱ ደስ ይለኛል ፍቅሩን ቀምሻለሁ በመከራዬ ቀን በእርሱ ድኛለሁ የዘለዓለም ደስ በእርሱ ማመኔ ነው ዓለሙም ንብረቱም ሁሉም ኃላፊ ነው /2/ ዘመን የማይሽረው ቀን የማይለውጠው የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ኃያል ነው ፍቃዱን ለማድረግ አምላክ ይመራኛል ሕጉም ለመንገዴ ብርሃን ሆኖኛል /2/ ጎብኝቶኛል አምላክ ድንቅ አድርጎልኛል በመስቀል ስቃዩ በደሙ ገዝቶኛል በእርሱ ደስ ይበለን እንቅረብ ከቤቱ አያልቅም ብዙ ነው የአምላክ በረከቱ /2/ ከቤትህ በረከት ስለሰጠኸኝ መዳንን በቃልህ ስላደረግክልኝ 28 ላመስግንህ እንጂ ሌላ ምን እላለሁ ከቤትህ ላልለይ ልቤን እሰጣለሁ /2/