ዘይክል ኲሎ ወአልቦ ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር አምላከ ነዳያን ረዳኤ ምንዱባን ንኅነ ሀቤከ /2/ ተማፀነ የድሆች አለኝታ ተስፋ ላጡ ተስፋ ሁሉንም የሚችል ደራሽ ለተገፋ ለእኛም ድረስልን በኃጢአት ሳንጠፋ አዝ . . . /ናዛዜ ኅዙናን/ ከገነት ሲባረር አዳም ተሳስቶ ባለቀሰ ጊዜ ልጅነቱን አጥቶ ትድናለህ ብለህ ያዳንከው በመስቀል የቅዱሳን አምላክ አቤቱ ቸል አትበል አዝ . . . /ወተስፋ ቅቡጻን/ ሕዝበ እስራኤልን ፈርኦን ሲገዛቸው ጭንቅና መከራ እያጸናባቸው በእነራሔል ልቅሶ ሙሴን ላክህላቸው አዝ . . . /ረዳኤ ምንዱባን/ እኛም ወገኖችህ ወደ አንተ እንጮሃለን ከጭንቅ ከመከራ እንድትታደገን ጌታ አንተ ነህና ናዛዜ ኅዙናን አዝ . . . /ናዛዜ ኅዙናን/ አዝ . . . /ወተስፋ ቅቡጻን/