ኑ የሕይወት እንጀራ እንብላ የሕይወት እንጀራ /2/ ለዘለዓለም በቤቱ አንኖራለን ድዉያነ ሥጋ ጸጋው የራቃችሁ በሥጋም በነፍስም ጽድቅ የተራባችሁ ለመዳኑ ሕይወት አምላክ ሲጠራችሁ በፍርሐት ቅረቡ ወደ ፈጣሪያችሁ አዝ .... ሥጋውን ፍሪዳ አድርጎ ሰጥቶናል ደሙን መጠጥ አድርጎ በፍቅር አድሎናል ከዚህ ሰፊ ማዕድ ቅረቡ ይለናል ከቅዱሳን ብረት ይቀላቅለናል አዝ .... ኑ ወደኔ ይላል የዓለሙ ሁሉ ቤዛ ጊዜአችን አይለፍ በዋዛ ፈዛዛ ሥጋውን ኝልበላን ንስሐ ገብተን ደሙንም ኝልጠጣን ከኃጢአት ርቀን በመጨረሻው ቀን ዕዳ አለብን አዝ ....