ማን እንደ እርሱ እንደ እግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር ሞገድና ነፋስ የሚtaዘዙለት አብሕርት ቀላያት የመሰከሩለት ቱም መቃብርን ሳይከፍት የተነሣ ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ አዝ . . . ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ የጸጋ ልብሳቸው ጽድቅን ለtaረዙ የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለድሃ አደግ አዝ . . . የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ ከባርነት ዓለም ከጽልመት ያወጣ ብርሃን ዘበአማን ጨለማን ያራቀ ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስtaረቀ አዝ . . . በመከራ ሳሉ ሕዝቦቹን ያሰበ ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበ ከባቴ አበሳ ምሕረቱ የበዛ ጌtaችን እርሱ ነው ሁላችን ቤዛ አዝ . . .