ዘምሩለት /4/ እስኪ ለአምላክ ተቀኙለት /2/ ስለክብሩ ቃኙ ሁልጊዜ አወድሱት ለፈጠረን አምላክ ስቡህ እንበልለት ዓለምን ፈጥሮልን እኛን እንዲደላን ምን እንከፍለዋለን እንበል ተመስገን አዝ .... ምድርን በአበባ ያስጌጠልን ለእኛ ብርሃን እንዳናጣ ፀሐይን ዳግመኛ ውኃ እንዳንጠማ ቀላያትን ፈጥሮ አድሎናልና እንዘምር በአንክሮ አዝ .... እስኪ ዘምሩለት እንደመላእክት እንደ አርባዕቱ እንስሳ ቀንና ሌሊት ክብርና ምስጋና ይገባዋል ለእርሱ እንዘምር በዕልል ገብተን ከመቅደሱ አዝ ....