መጽሐፍ ቅዱስን ሁሉም ያነበዋል ምዕራፍና ቁጥሩን ሁሉም ይጠቅሰዋል በዚህ ብቻ አይበቃም ተርጓሚ ያሻዋል እንደ ፈቃዳችን ብንተረጉመው/2/ በውጥን የሚያስቀር ስሕተቱ ብዙ ነው/2/ ከቶ በሰው ፈቃድ ትንቢት እንዳልመጣ ይመክረናል መጽሐፍ ከሕግ እንዳንወጣ እንጠይቅ መምህራን ያሉት በደረጃ /2/ እናንብብ መፃሕፍት ይሁኑን ማስረጃ/2/