አትልፊ በከንቱ አትድከሚ ዓለም/2/ ቆርጫለሁ እኔ ከጌ አልለይም/2/ እኔ አልገበዝም አልደለልም ልቤ እያወቀ አምላኬን አልክድም ዓለምን ለመምሰል እምነት አልለውጥም በከንቱ ማባበል ከመንገዱ አልወጣም አዝ .... ሥጋዊ ፍላጐት አያ ልለኝም ዓለማዊ እውቀት አያስ ብየኝም እነዚህ በአንድነት ይጠፋሉ ሁሉም የእግዚአብሔር ጽድቅ ግን ይኖራል ዘለዓለም። አዝ... ሰውን ለማስደሰት ትዕዛዙን አልጥስም 34 በከንቱ ማባበል ከመንገዱ አልወጣም ለዲያብሎስ እጄን በፍፁም አልሰጥም ጌ እግዚአብሔርን አላሳዝነውም አዝ .... ከቅዱስ እግዚአብሔር እኔ አልለይም በምድርም በሰማይ ያለእርሱ አልኖርም መመኪያዬ እርሱ ነው ባዝንም ብደስትም ሕይወቴ ጌ ነው ያለእርሱ አልኖርም። አዝ ....